የሕይወት ፡ ውኃ (Yehiwot Weha) - አብርሃም ፡ እና ፡ እያሱ ፡ ተክለማሪያም

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አብርሃም ፡ እና ፡ እያሱ ፡ ተክለማሪያም
(Abraham and Eyasu Teklemariam)

Abraham and Eyasu Teklemariam 2.jpg


(2)

ዘመናት ፡ አይለውጡህም
(Zemenat Aylewetuhem)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:13
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአብርሃም ፡ እና ፡ እያሱ ፡ ተክለማሪያም ፡ አልበሞች
(Albums by Abraham and Eyasu Teklemariam)

"በዚያም ፡ በታላቁ ፡ ቀን ፡ ኢየሱስ ፡ ቆሞ
'ማንም ፡ የተጠማ ፡ ቢኖር ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ይምጣና ፡ ይጠጣ
በእኔ ፡ የሚያምን ፡ መጽሐፉ ፡ እንዳለው
የሕይወት ፡ ውኃ ፡ ወንዝ ፡ ከሆዱ ፡ ይፈልቃል'
ዛሬም ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ፀሎታችን"


የእምነት ፡ ቃሉን ፡ የሰጠ ፡ እስከ ፡ ፍጻሜው ፡ ታማኝ ፡ ነው
የፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ አባት ፡ ለልጆቹ ፡ የሚዋጋው
እሩህሩህ ፡ አምላኬ ፡ የፍቅር ፡ ውኃ ፡ ምንጭ
ኃጢአት ፡ እንዳይጥለኝ ፡ ያዝከኝ ፡ በቸርነት
 
አዝ፦ የሕይወት ፡ ውኃ ፡ ምንጭ ፡ የነፍስ ፡ ሁሉ ፡ እረኛ
ያንቀላፋው ፡ ልቤ ፡ በውሃው ፡ ይነሳል
አፍስስ ፡ ቅዱስ ፡ መንፈስህን ፡ ለተጠማች ፡ ነፍሴ
ይፍለቅ ፡ ፍቅርህ ፡ ከሕይወቴ ፡ ይህ ፡ ነው ፡ ፀሎቴ
 
ማንም ፡ የተጠማ ፡ ቢኖር ፡ ወደኔ ፡ ይምጣ ፡ ብለሃል
የሕይወት ፡ ውኃ ፡ ወንዝ ፡ በሰው ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ ያድራል
የመንፈስ ፡ አንደበት ፡ የሰማያት ፡ እንባ
ፈሰሰ ፡ ከዓይኔ ፡ መቼም ፡ ላልጠማ
 
አዝ፦ የሕይወት ፡ ውኃ ፡ ምንጭ ፡ የነፍስ ፡ ሁሉ ፡ እረኛ
ያንቀላፋው ፡ ልቤ ፡ በውሃው ፡ ይነሳል (ማንም ፡ ለተጠማ ፡ የምትሰጥ ፡ እርካታ)
አፍስስ ፡ ቅዱስ ፡ መንፈስህን ፡ ለተጠማች ፡ ነፍሴ
ይፍለቅ ፡ ፍቅርህ ፡ ከሕይወቴ ፡ ይህ ፡ ነው ፡ ፀሎቴ
 
የሕይወት ፡ ውኃ ፡ ምንጭ ፡ በውኃው ፡ ይነሳል
አፍስስ ፡ ቅዱስ ፡ መንፈስህን