ላመስግነው ፡ አምላኬን (Lamesgenew Amlakien) - አብርሃም ፡ እና ፡ እያሱ ፡ ተክለማሪያም

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አብርሃም ፡ እና ፡ እያሱ ፡ ተክለማሪያም
(Abraham and Eyasu Teklemariam)

Abraham and Eyasu Teklemariam 2.jpg


(2)

ዘመናት ፡ አይለውጡህም
(Zemenat Aylewetuhem)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:41
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአብርሃም ፡ እና ፡ እያሱ ፡ ተክለማሪያም ፡ አልበሞች
(Albums by Abraham and Eyasu Teklemariam)

ምድርና ፡ ሞላዋን ፡ በቃልህ ፡ ያፀናህ
በክብርህ ፡ ሞገስ ፡ በብርሃንህ ፡ ዓለምን ፡ የሞላህ
እንዴት ፡ ላክብርህ ፡ ዛሬስ ፡ ምን ፡ ይዤ ፡ በፊትህ ፡ ልግባ
አዲስ ፡ ምሥጋና ፡ አዲስ ፡ ዝማሬ ፡ አይበዛብህምና

አዝ:- እጆቼን ፡ ወደ ፡ ሰማይ ፡ አንስቼ
በንጹህ ፡ ልብ ፡ ዛሬም ፡ እስከ ፡ ዘለዓለም
ላመስግነው ፡ አምላኬን ፡ በሰማይ ፡ ላለው
ለኢየሱስ ፡ ቅኔ ፡ ልቀኝለት (፪x)
ታማኝነቱንም ፡ ገናናነቱንም ፡ አይቼ
 
ስለ ፡ ምሕረትህ ፡ ባስብ ፡ ባወራ ፡ አመታት ፡ ያጥሩኛል
አቤቱ ፡ ኢየሱስ ፡ የታምራትህ ፡ ዘርፍ ፡ እረዝሟልና
ለነፍሴ ፡ ዘወትር ፡ ተሟግተሃል
ሕይወቴንም ፡ በደምህ ፡ ተቤዥተሃልና
 
አዝ:- እጆቼን ፡ ወደ ፡ ሰማይ ፡ አንስቼ
በንጹህ ፡ ልብ ፡ ዛሬም ፡ እስከ ፡ ዘለዓለም
ላመስግነው ፡ አምላኬን ፡ በሰማይ ፡ ላለው
ለኢየሱስ ፡ ቅኔ ፡ ልቀኝለት (፬x)
ታማኝነቱንም ፡ ገናናነቱንም ፡ አይቼ
 
በላይ ፡ በዙፋንህ ፡ ላይ
በክብር ፡ ነግሰህ ፡ ታየህ ፡ አቤቱ (፬x)
(ክብር ፡ ይሁን)

ላመስግነው ፡ አምላኬን
በሰማይ ፡ ላለው ፡ ለኢየሱስ
ቅኔ ፡ ልቀኝለት (፪x)

በላይ ፡ በዙፋንህ ፡ ላይ
በክብር ፡ ነግሰህ ፡ ታየህ ፡ አቤቱ
(ክበር ፡ ክበር ፡ መድኃኒቴ)
በላይ ፡ በዙፋንህ ፡ ላይ
በክብር ፡ ነግሰህ ፡ ታየህ ፡ አቤቱ
(ክበር ፡ ንገሥ ፡ መድኃኒቴ)(፪x)
በላይ ፡ በዙፋንህ ፡ ላይ
በክብር ፡ ነግሰህ ፡ ታየህ ፡ አቤቱ