ግሩሙ ፡ ኢየሱስ (Girumu Eyesus) - አብርሃም ፡ እና ፡ እያሱ ፡ ተክለማሪያም

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አብርሃም ፡ እና ፡ እያሱ ፡ ተክለማሪያም
(Abraham and Eyasu Teklemariam)

Abraham and Eyasu Teklemariam 2.jpg


(2)

ዘመናት ፡ አይለውጡህም
(Zemenat Aylewetuhem)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 4:31
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአብርሃም ፡ እና ፡ እያሱ ፡ ተክለማሪያም ፡ አልበሞች
(Albums by Abraham and Eyasu Teklemariam)

እኔ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ሳልመጣ
ገና ፡ ኃጢአተኛ ፡ ሳለሁ
ፍቅርህ ፡ ለእኔ ፡ ተገለጠ
በፀጋህ ፡ ድኛለሁ

አዝ:- ግሩሙ ፡ ኢየሱስ ፡ መድኃኒቴ
ግሩሙ ፡ ኢየሱስ ፡ ይገርመኛል
ግሩሙ ፡ ኢየሱስ ፡ ከጥፋቴ
ግሩሙ ፡ ኢየሱስ ፡ አድኖኛል

(ይገርመኛል ፡ ኢየሱስ.....ለኔ ፡ ያለው ፡ ፍቅር.....ሃሌሉያ)

አንተ ፡ ለነፍሴ ፡ መቸገር ፡ አልነበረብህም
ግን ፡ አምላኬ ፡ በኔ ፡ ፍቅር
ነፍሴን ፡ ችላ ፡ አላልካትም
 
አዝ:- ፈቃዱ ፡ ኢየሱስ ፡ የኔ ፡ ጌታ
ፈቃዱ ፡ ኢየሱስ ፡ አፍቅሮኛል
ፈቃዱ ፡ ኢየሱስ ፡ የኔ ፡ አለኝታ
ፈቃዱ ፡ ኢየሱስ ፡ ለውጦኛል ፡
 
(ነፍሴ ፡ ወደደችህ.....ግሩሙ ፡ ኢየሱስ
ነፍሴ ፡ ወደደችህ.....ሃሌሉያ(፪x))
 
የሰማይን ፡ ዕርዝመት ፡ ያወቅህ ፡ የመረመርከው
የምድርን ፡ ሚስጥር ፡ የያዝክ
እኔን ፡ የፈጠርከው
 
አዝ:- ታጋሹ ፡ ኢየሱስ ፡ ቻዩ ፡ ጌታ
ታጋሹ ፡ ኢየሱስ ፡ ታግሶኛል
ታጋሹ ፡ ኢየሱስ ፡ ብበድልም
ታጋሹ ፡ ኢየሱስ ፡ አንጽቶኛል

(ይገርመኛል ፡ ኢየሱስ.....ለኔ ፡ ያለው ፡ ፍቅር.....ሃሌሉያ)

ግሩሙ ፡ ኢየሱስ ፡ መድኃኒቴ
ግሩሙ ፡ ኢየሱስ ፡ ይገርመኛል
ግሩሙ ፡ ኢየሱስ ፡ ከክፋቴ
ግሩሙ ፡ ኢየሱስ ፡ አድኖኛል
 
ፈቃዱ ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ፈቃዱ ፡ ኢየሱስ ፡ አፍቅሮኛል
ፈቃዱ ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ
ፈቃዱ ፡ ኢየሱስ ፡ ለውጦኛል

ታጋሹ ፡ ኢየሱስ ፡ ቻዩ ፡ ጌታ
ታጋሹ ፡ ኢየሱስ ፡ ታግሶኛል
ታጋሹ ፡ ኢየሱስ ፡ ብበድልም
ታጋሹ ፡ ኢየሱስ ፡ አንጽቶኛል