በሚመራኝ ፡ እሄዳለሁ (Bemimeragn Ehiedalew) - አብርሃም ፡ እና ፡ እያሱ ፡ ተክለማሪያም

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አብርሃም ፡ እና ፡ እያሱ ፡ ተክለማሪያም
(Abraham and Eyasu Teklemariam)

Abraham and Eyasu Teklemariam 2.jpg


(2)

ዘመናት ፡ አይለውጡህም
(Zemenat Aylewetuhem)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6:09
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአብርሃም ፡ እና ፡ እያሱ ፡ ተክለማሪያም ፡ አልበሞች
(Albums by Abraham and Eyasu Teklemariam)

በሚመራኝ ፡ እሄዳለሁ
ህይወቴን ፡ ሰጥቼዋለሁ
አልረሳም ፡ አስታዉሳለሁ
በሞቱ ፡ ተፈውሻለሁ

አዝ:- በሌት ፡ በቀኔ ፡ ይመራኛል
ኢየሱስ ፡ ያስፈልገኛል
እውነተኛ ፡ ወዳጄ ፡ ነው
ነፍሴን ፡ በደሙ ፡ የገዛው

ትዕዛዝህን ፡ አከብራለሁ
በክንድህ ፡ እደገፋለሁ
ተስፋ ፡ ሳልቆርጥ ፡ እጓዛለሁ
አንድ ፡ ቀን ፡ አዳኜን ፡ አየዋለሁ
                                                      
አዝ:- በሌት ፡ በቀኔ ፡ ይመራኛል
ኢየሱስ ፡ ያስፈልገኛል
እውነተኛ ፡ ወዳጄ ፡ ነው
ነፍሴን ፡ በደሙ ፡ የገዛት
 
አልተክዝም ፡ ከቶ ፡ አልፈራም
አንተ ፡ ካለህ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
ፍጹም ፡ ፍቅርህ ፡ መድኃኒቴ
ማጽናኛ ፡ ነው ፡ ለሕይወቴ
 
አዝ:- በሌት ፡ በቀኔ ፡ ይመራኛል
ኢየሱስ ፡ ያስፈልገኛል
እውነተኛ ፡ ወዳጄ ፡ ነው
ነፍሴን ፡ በደሙ ፡ የገዛት

አንዳንድ ፡ ጊዜ ፡ ፈተና ፡ ሲበዛ
መከራ ፡ ችግር ፡ ቢበዛብን
(ኧረ) ፡ አንድ ፡ እንኳ ፡ ቢታጣ ፡ የሚረዳ

ኢየሱስ ፡ አለ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ
አንዳንድ ፡ ጊዜ ፡ ፈተና ፡ ሲበዛ ፡ (ሃሌሉያ)
መከራ ፡ ችግር ፡ ቢበዛብን
አንድ ፡ እንኳ ፡ ቢታጣ ፡ የሚረዳ ፡ (ቢታጣ)
ኢየሱስ ፡ አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ (፫x)