ክብሬ ፡ ነው (Kebrie New) - አቤነዘር ፡ ታገሰ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አቤነዘር ፡ ታገሰ
(Abenezer Tagesse)

Lyrics.jpg


(Volume)

ነጠላ ፡ መዝሙሮች
(Singles)

ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአቤነዘር ፡ ታገሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Abenezer Tagesse)

የሕይወቴ ፡ ክብር ፡ የሕይወቴ ፡ ቤዛ
የዘላለም ፡ ክብሬ ፡ ነው ፡ የሕይወቴ ፡ መዓዛ
ከእኔ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ ምንም ፡ ሳይኖረኝ
እንዲሁ ፡ በፍቅር ፡ በፀጋው ፡ ዳንኩኝ(፪)

እስኪ ፡ ንገረኝ ፡ ምን ፡ ሰርቶልህ ፡ ነው
ምሕረት ፡ ፍቅር ፡ ፀጋ ፡ የምትለው
በዘመን ፡ ጊዜ ፡ በዓመታት ፡ ሁሉ
ያልተሰማ ፡ ነው ፡ የምትለው ፡ ሁሉ

አምላክ ፡ እንዲሁ ፡ ሰውን ፡ ወደደ
ለእኔ ፡ እና ፡ ለአንቺ ፡ ማለደ
ፍቅር ፡ ነው ፡ ፍቅር ፡ ነው
ከላይ ፡ ያስወረደው
እኔ ፡ በራሴ ፡ ከምን ፡ ልበቃ
አድኖኝ ፡ እንጂ ፡ በፀጋ
ፍቅር ፡ ነው ፡ ፀጋ ፡ ነው
እኔን ፡ የሚያኖረኝ

ፍቅር ፡ ነው ፡ ኑሮዬ
ፍቅር ፡ ነው ፡ ደስታዬ
ፍቅር ፡ ነው ፡ የሚያኖረኝ
ፍቅር ፡ ነው ፡ ያከበረኝ

ፍቅር ፡ ነው ፡ ሕይወቴ
ፍቅር ፡ ነው ፡ ማጀቴ
ፍቅር ፡ ነው ፡ ኑሮዬ
ፍቅር ፡ ነው ፡ ዘላለሜ

የሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ነው ፡ የተጠጋው ፡ ያርፋል
የዘላለም ፡ ቤት ፡ ነው ፡ ከሲዖል ፡ ያድናል
እርሱ ፡ መዳኛ ፡ ነው ፡ የሞተው ፡ ሕይወት
እውነት ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ አይደለም ፡ ቅዠት

ክብሬ ፡ ነው ፡ ውበቴ
ጌጤ ፡ ነው ፡ ሽልማቴ

በእርሱ ፡ አረፍኩኝ ፡ ለዘላለም
ኢየሱሴ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ዓለም
በእርሱ ፡ ብርሃን ፡ ሆነ ፡ ቤቴ
ጨለማ ፡ የለም ፡ በሕይወቴ

ክብሬ ፡ ነው ፡ ውበቴ
ጌጤ ፡ ነው ፡ ሽልማቴ

በእርሱ ፡ አረፍኩኝ ፡ ለዘላለም
ኢየሱሴ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ዓለም
በእርሱ ፡ ብርሃን ፡ ሆነ ፡ ቤቴ
ጨለማ ፡ የለም ፡ በሕይወቴ