ስለስምህ (Selesemeh) - አቤነዘር ፡ ታገሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አቤነዘር ፡ ታገሰ
(Abenezer Tagesse)

Abenezer Tagesse 1.jpg


(1)

ኢየሱስ ፡ አለ
(Eyesus Ale)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

፲ ፭ (15)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአቤነዘር ፡ ታገሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Abenezer Tagesse)

አዝ፦ ስለስምህ ፡ መልካምነት ፡ ማን ፡ ተናግሮ ፡ ይዘልቃል
ከተባለው ፡ በጐነትህ ፡ ያልተባለው ፡ በዝቷል
በሄድኩበት ፡ የምጠራው ፡ የአንተ ፡ ስምማ
አጠገቤ ፡ ብቻ ፡ ሳይሆን ፡ ለሩቁም ፡ ይሰማ (፪x)

ኢየሱስ (፪x) ፡ ባልንበት ፡ ኧረ ፡ ስንቱ ፡ ተሰራበት
ማረኝ ፡ ብለው ፡ ያለቀሱ ፡ ስለስምህ ፡ ተፈወሱ (፪x)

ስምህን ፡ ስጠራ ፡ ሁሌ ፡ የማስበው
ትልቁ ፡ ተራራ ፡ ሜዳ ፡ እንደሚሆን ፡ ነው
አክብደው ፡ ያዩትን ፡ የሕይወት ፡ መንገድ
ስምህ ፡ ባለፈበት ፡ ማይሄደው ፡ ሲሄድ

ኢየሱስ ፡ የነፍሴ ፡ መዳኛ
ኢየሱስ ፡ የኑሮዬ ፡ ዳኛ
ኢየሱስ ፡ የሕይወት ፡ አክሊሌ
ኢየሱስ ፡ ሰማያዊ ፡ ክብሬ (፪x)

አዝ፦ ስለስምህ ፡ መልካምነት ፡ ማን ፡ ተናግሮ ፡ ይዘልቃል
ከተባለው ፡ በጐነትህ ፡ ያልተባለው ፡ በዝቷል
በሄድኩበት ፡ የምጠራው ፡ የአንተ ፡ ስምማ
አጠገቤ ፡ ብቻ ፡ ሳይሆን ፡ ለሩቁም ፡ ይሰማ (፪x)

ኢየሱስ (፪x) ፡ ባልንበት ፡ ኧረ ፡ ስንቱ ፡ ተሰራበት
ማረኝ ፡ ብለው ፡ ያለቀሱ ፡ ስለስምህ ፡ ተፈወሱ (፪x)

የአንተን ፡ መልካምነት ፡ ይዩ ፡ ወንድሞቼ
አላፈርኩምና ፡ ስምህን ፡ ጠርቼ
በበጐ ፡ ተጠሪ ፡ ክፋት ፡ የማያውቀው
መልካሙ ፡ እረኛ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው

ኢየሱስ ፡ የነፍሴ ፡ መዳኛ
ኢየሱስ ፡ የኑሮዬ ፡ ዳኛ
ኢየሱስ ፡ የሕይወት ፡ አክሊሌ
ኢየሱስ ፡ ሰማያዊ ፡ ክብሬ (፪x)

ኢየሱስ (፫x) ፡ ኢየሱስ ፡ ሰማያዊ ፡ ክብሬ

ኢየሱስ ፡ የነፍሴ ፡ መዳኛ
ኢየሱስ ፡ የኑሮዬ ፡ ዳኛ
ኢየሱስ ፡ የሕይወት ፡ አክሊሌ
ኢየሱስ ፡ ሰማያዊ ፡ ክብሬ

ኢየሱስ (፭x)