Abenezer Legese/Nafekialehu/Eyesus

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

{{ አልቻልኩም እኔ ስለ ኢየሱስ ዝም ማለት ኧረ እኔ አልቻልኩም እኔ ስለ ኢየሱስ ዝም ማለት

አመስግን  ይለኛል  ውስጤ
በል  ዘምር  ይለኛል  ውስጤ
አምልከው  ይለኛል  ውስጤ
ውለታ  አለብህ  ይለኛል
መች  ያስችለኛል x2
ውስጤ  አለ  ዕልልታ x4
የማሰማው  ለጌታ
ውስጤ  አለ  ምሥጋና x4
የምዘምርው  ገና
ነብሴ አጥንቴ ዉስጥ ይሰማኛል
የሱስ ሲባል ውስጤ ይዘላል 
ከቶ አልችል እኔ ዝም ማለት
እሱ ሲመለክ ቆሞ ማየት 
ፍቅሩ በውስጡ  እያቃጠለው 
ይውጣልኝ የሚል ውስጤ ያለው 
እንደኔ ያለ ከቶ ያልቻለ 
ኢየሱስ ይበል እየጮኸ  
ኢየሱስ x3  ኢየሱስ x3
ውስጤ ነደደ - ኢየሱስ x3
በፍቅሩ ብዛት - ኢየሱስ x3
ዝም አያሰኝ - ኢየሱስ x3
ጌታ ያረገልኝ - ኢየሱስ x3 
በአብ ልክ ያለ ልኡል አምላክ ነው
የጌቶች ጌታ ሀያል ንጉስ ነው 
እልፍ አእላፍ መላክት ሚሰግዱለት
ዙፋኑ ፅኑ መይናወጥ
ታድያ ይሄ ጌታ ሰዉ ሲሆን ወርዶ 
ሀጥያቴን ሲሽር በመስቀል ሞቶ 
በሰማይ ስፍራ ሲያስቀምጠኝ 
በቃ ይሄ ነው ያላስቻለኝ
ኢየሱስ x3 ኢየሱስ x3
ከሙታን መንደር - ኢየሱስ x3
ስሜን ሰረዘው - ኢየሱስ x3
በህያዋን አገር - ኢየሱስ x3
በሰማይ ፃፈው - ኢየሱስ x3

ኢየሱስ ነው x4
ያከበረኝ ሰው ያረገኝ እመሰክራለው 
ኢየሱስ ነው x4
ያከበረኝ ሰው ያረገኝ እመሰክራለው 
ውስጤ  አለ  ዕልልታ x4
የማሰማው  ለጌታ
ውስጤ  አለ  ምሥጋና x4
የምዘምርው  ገና