አቤኔዘር ፍቅሩ (Abenezer Fikru)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ



ስምህ ታትሟል በልቤ አይጠፋም ከአንደበቴ

ወደድኩት ከምንም በላይ ጣፈጠኝ ስጠራው አፌ ላይ ×2


እየሱስ በሞት እና በኔ

እየሱስ ሲቀር አንድ እርምጃ

እየሱስ አበቃለት ሲባል

እየሱስ ስምህ ጣልቃ ገባ

እየሱስ ዛሬ ሁሉም አልፎ

እየሱስ ቆሜ ብዘምር

እየሱስ ያንሳል እንጂ አይበዛም

እየሱስ ለስምህ ክብር

እየሱስ እየሱስ ስምህ መድሃኒቴ ×4


ለሊቱ እጅግ በርትቶ አይመስልም ነበር የሚነጋ

ዛሬማ መጨረሻው ነው አይ የኔ ነገር አበቃ

ደጉ ሳምራዊ እየሱስ ማረኝ ስል የዳዊት ልጅ

ህመሜ ተሰምቶት ቆመ ዳሰሰኝ በፍቅር እጅ


ተፈውሼ ቀረሁ ሄደ ላይመለስ

ስምህ በነፃ ቸረኝ ለሰውነቴ ፈውስ

ገንዘብ ለሁሉም ነገር መልስ ልሆን አይችልም

በኢየሱስ ስም ፊት ግን አረ ማንም አይቆምም


እየሱስ እየሱስ ስምህ መድሃኒቴ ×4


ስምህ ታትሟል በልቤ አይጠፋም ከአንደበቴ

ወደድኩት ከምንም በላይ ጣፈጠኝ ስጠራው አፌ ላይ ×2


እየሱስ በሞት እና በኔ

እየሱስ ሲቀር አንድ እርምጃ

እየሱስ አበቃለት ሲባል

እየሱስ ስምህ ጣልቃ ገባ

እየሱስ ዛሬ ሁሉም አልፎ

እየሱስ ቆሜ ብዘምር

እየሱስ ያንሳል እንጂ አይበዛም

እየሱስ ለስምህ ክብር

እየሱስ እየሱስ ስምህ መድሃኒቴ ×4


ከተወለደ ጀምሮ በቤተመቅደስ ደጅ

ተቀምጦ የኖሬ እያየ የሰው እጅ

እንደለመደው በቀትር ልመና ላይ ባለበት

የስምህን ሀይል ይዘው አገኙት ሐዋርያት

ብርና ወርቅ የለንም ያለንን እንስጥህ

ስሙ ነው ያሰረህን ፈቶ የሚያቆምህ

ገንዘብ ለሁሉም ነገር መልስ አይሆንም

በኢየሱስ ስም ፊት ግን አረ ማንም አይቆምም


እየሱስ እየሱስ ስምህ መድሃኒቴ ×4