ስጦታዎቼ (Sitotawoche) - ገዛኸኝ ሙሴ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ገዛኸኝ ሙሴ
(ገዛኸኝ ሙሴ)

Lyrics.jpg


(1)

አልበም
(1)

ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የገዛኸኝ ሙሴ ፡ አልበሞች
(Albums by ገዛኸኝ ሙሴ)

ስጦታዎቼ ከአምላኬ ያገኘኋችሁ
እደጉ ልጆቼ ኢየሱስ ያሳድጋችሁ
ከዘመኑ አመጽ በደሙ ጋርዶ ያውጣችሁ
ለኔ እንደ ቆመ ፤ ለእናንተም ይቁምላችሁ

አደራ ናችሁ ከእግዚሃብሄር ወደ እኔ የተላካችሁ
ስሙን በእናንተ እንዳነግስ ፍቅሩንም እንዳሳያችሁ
የፍቅሩ መገለጪያዬ የአምላኬ ልዩ ስጦታ
ለዘላለሙ ይባረክ እናንተን የሰጠኝ ጌታ
ግሩም ነው ጌታ አሰራሩ እናንተን ብቻ መች ሰጠ
ፍቅርንም በውስጤ አኑሯል እንድወዳችሁ ሚያስችለኝ
ለናንተ ያለኝን ፍቅር ሳይ ፍጹም ፍቅሩን አስባለሁ
ቸርነት ምህረቱ ታውሶኝ የፍቅር እንባ አነባለሁ

ስጦታዎቼ ከአምላኬ ያገኘኋችሁ
እደጉ ልጆቼ ኢየሱስ ያሳድጋችሁ
ከዘመኑ አመጽ በደሙ ጋርዶ ያውጣችሁ
ለኔ እንደ ቆመ ፤ ለእናንተም ይቁምላችሁ

ፍቅራችሁ ትዝታዬ ነው፤ እርቄ በሄድኩኝ ጊዜ
ሳላያችሁ ውዬ ካደርኩ ልቤ ይሰማዋል ትካዜ
ሳቃችሁ ብቻም አይደለም ይናፍቀኛል ለቅሷችሁ
ፀጥታው ይጮህብኛል ለአፍታ ከፊቴ ሳጣችሁ
እውነቱን ነግራችኋለሁ ፍርሃትም አለ በውስጤ
ዘመኑ እየከፋ ሲሄድ እየጨመረ ነው ምጤ
አደራ ሰጥቶኛል እና በእርሱ ስራዓት እንድታድጉ
ከዘመኑ አመፅ ለማምለጥ ልጆቼ አምላክን ፈልጉ

ስጦታዎቼ ከአምላኬ ያገኘኋችሁ
እደጉ ልጆቼ ኢየሱስ ያሳድጋችሁ
ከዘመኑ አመጽ በደሙ ጋርዶ ያውጣችሁ
ለኔ እንደ ቆመ ፤ ለእናንተም ይቁምላችሁ