እንደ ሰው

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ያየናል የማያይ ሲመስል ይሰማናል በብርቱ ዝም ሲል አለ የሚረዳን በዙፋኑ ሚደርስልን በማዳኑ

በድካማችን ሚራራልን የማይስቅ በውድቀታችን በሐዘናችን የሚጽናናን ኢየሱስ አለን ሚያበረታን

በሕመማችን ሚራራልን የማይስቅ በውድቀታችን በሐዘናችን የሚያጽናናን ኢየሱስ አለን ሚያበረታን

እርሱ ራሱ እንደ ሰው ተፈትኖ ብዙ አልፎበታል ሰውን ሆኖ ከኃጢአት በቀር ብዙ ሆኗል ምናልፍበት ይገባዋል

እርሱ ራሱ እንደ ሰው ተፈትኖ ብዙ አልፎበታል እኛን ሆኖ ከኃጢአት በቀር ብዙ ሆኗል ምናልፍበት ይገባዋል

ይራራልናል ያስብልናል በጊዜው ሠርቶ ደግሞም ያስቀናል ይመጣል ነገ ዛሬም ያልቅና ደግሞ እንስቃለን ቆመን በትናንትና ደግሞ እንቆማለን በአዲስ ምስጋና በአዲስ ዝማሬ በአዲሱ ዜማ

ይራራልናል ያስብልናል በጊዜው ሠርቶ ደግሞም ያስቀናል ይመጣል ነገ ዛሬም ያልፍና ደግሞ እንስቃለን ቆመን በትናንትና ደግሞ እንቆማለን በአዲስ ምስጋና በአዲስ ዝማሬ በአዲሱ ዜማ

በጊዜው በሚያልፍ መከራ ብናልፍም ተራ በተራ የማይጥል ጌታን ይዘናል ልባችን በእርሱ ይጽናናል በጸጋው ስንቱን ተወጥተናል በወጀብ ሰላም ሆነናል ያልተወን ጌታ ይመስገን በእረፍቱ ከቦ የያዘን

ምንም ብናልፍ በዚህ ዓለም ፈተና አይለወጥም ለርሱ ያለን ምስጋና በመስቀሉ ያለፈውን እያየን በእምነታችን ዛሬም እንጸናለን

ይራራልናል ያስብልናል በጊዜው ሠርቶ ደግሞም ያስቀናል ይመጣል ነገ ዛሬም ያልቅና ደግሞ እንስቃለን ቆመን በትናንትና ደግሞ እንቆማለን በአዲስ ምስጋና በአዲስ ዝማሬ በአዲሱ ዜማ

ይራራልናል ያስብልናል በጊዜው ሠርቶ ደግሞም ያስቀናል ይመጣል ነገ ዛሬም ያልፍና ደግሞ እንስቃለን ቆመን በትናንትና ደግሞ እንቆማለን በአዲስ ምስጋና በአዲስ ዝማሬ በአዲሱ ዜማ

ጻድቅ ጌታ እንደ ሰው ተፈትኖ ብዙ አልፎበታል ሁሉን ሆኖ ከኃጢአት በቀር ብዙ ሆኗል ምናልፍበት ይገባዋል