አንተ ምስጋናዬ ነህ
አዝ:- አንተ ምስጋናዬ ነህ(*3) በአመታት
አንተ ምስጋናዬ ነህ(*3) በዘመናት
1) ክፉ ሲመጣ ያመለጥኩብህ
ስጣል ስረሳ የታሰብኩብህ ባንተ እዚህ ደረስኩ ከኔ ጋር ሆነህ ኢየሱስ ለኔ ምስጋናዬ ነህ
አዝ:-
2) አይኔ አየችህ አትደክምም በኔ
ባልመችህም ሰው በመሆኔ ምስጋናን ላውጅ በቤትህ ዙሪያ ነብሴ ትባርክህ ቆማ እንደገና
አዝ:-
3) በጠላቴ ፊት ሞገስ ሆንክልኝ
በእሳት መካከል አረማመድከኝ ባንተ ተደገፍኩ ምርኩዝ ሆንክልኝ አሜን ኢየሱስ ተባረክልኝ
አዝ:-
4) በድካም ጎኔ አንተ ቆምክልኝ
ጠላቴን ታግለህ አሸነፍክልኝ የት ያገኘኛል ተሻግሪያለሁ ካንተ የተነሳ በአብ ቀኝ አለሁ