አባል:YeabsiraDesta

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

በምስጋና ላይ እጨምራለው ምስጋና (Bemisgana Lay Echemeralehu Misgana)
[edit]

Bethlehem Wolde Lyrics


በምስጋና ላይ ፣ እጨምራለው ምስጋና
በምስጋና ላይ ፣ እጨምራለው ምስጋና
ፍቅሩ ማርኮኛል ፣ ም′ረቱ ያዘምረኛል
ፍቅሩ ማርኮኛል ፣ ም'ረቱ ያዘምረኛል

አቤቱ አምላኬ ሆይ ፣ ለሃይልህ እቀኛለው
ጠዋት ማታ ሁሌ ላንተ ፣ ክብርን እሰጣለው
በምህረትህ ማልዶ ጌታ ፣ ደስ ደስ ይለኛል
ምህረትህ ስላቆመኝ ፣ አመስግኝ ይለኛል

ዛሬም እጨምራለው ፣ የኔ ጌታ ክበር
ነገም እጨምራለው ፣ የኔ ጌታ ንገስ
ዛሬም እጨምራለው ፣ የኔ ጌታ ክበር
ነገም እጨምራለው ፣ የኔ ጌታ ንገስ

በምስጋና ላይ ፣ እጨምራለው ምስጋና
በምስጋና ላይ ፣ እጨምራለው ምስጋና
ፍቅሩ ማርኮኛል ፣ ም′ረቱ ያዘምረኛል
ፍቅሩ ማርኮኛል ፣ ም'ረቱ ያዘምረኛል

ሁል ጊዜ ክብርህንና ፣ ግርማ'ን አወራለው
ምህረትህን ለዘለዓለም ፣ እዘምረዋለሁ
ሰው በፈቃዱ ሳይገደድ ፣ ያመስግንሃል
ምህረትህ እግዚያብሔር ሆይ ፣ መቼ ዝም ያስብላል

ዛሬም እጨምራለው ፣ የኔ ጌታ ክበር
ነገም እጨምራለው ፣ የኔ ጌታ ንገስ
ዛሬም እጨምራለው ፣ የኔ ጌታ ክበር
ነገም እጨምራለው ፣ የኔ ጌታ ንገስ

ነብሴን ከማጥ አይኔን ከዕንባ ፣ ጠብቀሃልና
ስሜንም በህይወት መዝገብ ፣ ፅፈ′ልኛልና
ያረግክልኝን እያስብኩ ፣ ስለ አንተ አወራለው
ማርኮ ስለያዘኝ ፍቅርህ ፣ አዜምልሃለው

ዛሬም እጨምራለው ፣ የኔ ጌታ ክበር
ነገም እጨምራለው ፣ የኔ ጌታ ንገስ
ዛሬም እጨምራለው ፣ የኔ ጌታ ክበር
ነገም እጨምራለው ፣ የኔ ጌታ ንገስ

በምስጋና ላይ ፣ እጨምራለው ምስጋና
በምስጋና ላይ ፣ እጨምራለው ምስጋና
ፍቅሩ ማርኮኛል ፣ ም′ረቱ ያዘምረኛል
ፍቅሩ ማርኮኛል ፣ ም'ረቱ ያዘምረኛል

ባከብርህ እግዚያብሔር ሆይ ፣ ብዙ ምክንያት አለኝ
በአንተ ዘንድ መልካም ነገር ፣ ስለተደረገልኝ
አለም ሳይፈጠር ያኔ ፣ መርጠኸኛልና
እንዳከብርህ ደቀ-መዝሙር ፣ አርገኸኛልና

ዛሬም እጨምራለው ፣ የኔ ጌታ ክበር
ነገም እጨምራለው ፣ የኔ ጌታ ንገስ
ዛሬም እጨምራለው ፣ የኔ ጌታ ክበር
ነገም እጨምራለው ፣ የኔ ጌታ ንገስ

እስካ′ላም ፍጻሜ ፣ ከእናንተ ጋር ሆናለሁ
ብለህ እንደተናገርክ ፣ ቃልህን ፈፀምከው
በተራራ ቢሆን ፣ ደግሞ በሸለቆ
አብረኸን ሆነሃል አምናለሁ እንደ ስምህ ፣ እኛም አይተንሃል

ታማኝ ነህ ፣ እንደ ስምህ
ፍቅር ነህ ፣ እንደ ስምህ
እዉነት ነህ ፣ እንደ ስምህ ፣ እንደ ስምህ ኣሜን

ታማኝ ነህ ፣ እንደ ስምህ
ፍቅር ነህ ፣ እንደ ስምህ
እዉነት ነህ ፣ እንደ ስምህ ፣ እንደ ስምህ አሜን

(እንደስምህ ፣ እንደስምህ ፣ እንደስምህ ፣ እንደስምህ ኣሜን)
(እንደስምህ ፣ እንደስምህ)

38 አመት ፣ አልጋ ላይ የተኛውን
ሠው የለኝም ብሎ ፣ ተስፋ የቆረጠውን
ያለበት ድረስ ፣ ሄደህ ፈውስሃል
አዳኝ ነህ የኛ ጌታ እየሱስ እንደ ስምህ ፣ እኛም አይተንሃል

ፈዋሽ ነህ ፣ እንደስምህ
ሠላም ነህ ፣ እንደስምህ
ረዳት ነህ እንደስምህ ፣ እንደስምህ አሜን

ፈዋሽ ነህ ፣ እንደስምህ
ሠላም ነህ ፣ እንደስምህ
ረዳት ነህ እንደስምህ ፣ እንደስምህ አሜን

ከስም ሁሉ በላይ ፣ ስምን ተሰጥቶሃል
የሲኦልንም ቁልፍ ፣ በእጅህ ይዘሃል
ፍጥረታትም ሁሉ ፣ ይንበረከካሉ
ለታላቁ ስምህ ፣ ክብርን ይሰጣሉ

ጌታ ነህ ፣ እንደስምህ
አምላክ ነህ ፣ እንደስምህ
ገናና እንደስምህ ፣ እንደስምህ ኣሜን

ጀግና ነህ ፣ እንደስምህ
ንጉስ ነህ ፣ እንደስምህ
ኤልሻዳይ እንደስምህ ፣ እንደስምህ ኣሜን