አባል:Solomon degefe
- የማዕዘን ድንጋይ ለቤቴ
- መሠረት ምሶሶ ለህይወቴ
- ኢየሱስ ኢየሱስ የመቆሚያ አለቴ: X2
ዝቅ ያለው ከፍ ሲል ከፍም ያለው ዝቅ
የኔ ጌታ ኢየሱስ ቸርነቱ አያልቅ
ክንዱን እያየሁኝ እስከዛሬ አለሁኝ
ድንቁን እያወራሁ ገና እኖራለሁኝ X2
- የማዕዘን ድንጋይ ለቤቴ
- መሠረት ምሶሶ ለህይወቴ
- ኢየሱስ ኢየሱስ የመቆሚያ አለቴ: X2
ነፋሱ ሲነፍስ ጎርፉም ሲተባበር
የቀረበ ሲመስል ታንኴዬም ሊሰበር
አንት ወጀብ ማዕበል ዝም በል ጸጥ በል
ብሎ እየገሰጸልኝ ስንቱን አሻገረኝ X2
- የማዕዘን ድንጋይ ለቤቴ
- መሠረት ምሶሶ ለህይወቴ
- ኢየሱስ ኢየሱስ የመቆሚያ አለቴ: X2
ገሞራው ገንፍሎ የዲያቢሎስ ቁጣ
ትውልድ ሲተራመስ ሰው መሄጃ ሲያጣ
ፍርሃት አያርደኝ ክንፉ እሚጋርደኝ
አለኝ በክፉ ቀን አባት የሚወደኝ X2
- የማዕዘን ድንጋይ ለቤቴ
- መሠረት ምሶሶ ለህይወቴ
- ኢየሱስ ኢየሱስ የመቆሚያ አለቴ: X2
ኃጢአት ሲያቆሽሸኝ ደሙን እየረጨኝ
ምድረ በዳም ሲሆን ምንጭ እያመነጨ
ስታመም ሐኪም ፈውሴ ሲበርደኝ ፀጋ ልብሴ
ሌላ ምንም የለኝ ምስጋና ነው መልሴ X2
- የማዕዘን ድንጋይ ለቤቴ
- መሠረት ምሶሶ ለህይወቴ
- ኢየሱስ ኢየሱስ የመቆሚያ አለቴ: X2
በዩቲዩብ ለማዳመጥ ይህን አድራሻ ራይት ክሊክ አድርገው Open link in new tab የሚለውን ይጫኑ፡ https://www.youtube.com/watch?v=2aHqNeIXlFM