አባል:Nemowikimezmur
የትምወርቅ ደበበ
ስላላየሁት ጥበቃ
ሳላውቅ ሳልሰማ ሳላይ ሳላውቅ ሳልሰማ ሳላይ
ስንት ጊዜ አዳንከኝ ከጠላቶቼ ቀስት ታደከኝ
ስንት ጊዜ አዳንከኝ ወጥመድን በመስበር ረዳኸኝ
ስላላየሁት ምህረት ስላላየሁት ጥበቃ ሳለላየሁት እርዳታ ክበር የኔ ጌታ ፡፡ 2X
ስወጣ ስገባ አይኖችህ ያዩኛል
ክፉ እንዳይነካኝ ይንከባከቡኛል ይንከባከቡኛል
በዙሪያ ቢዞር ጠላቴ ያላገኘኝ
ምህረት ቸርነትህ ሁሌ እየከበበኝ ሁሌ እየከበበኝ
ቅጥር ነህ ለኔ ጋሻ ነህ ለኔ ከለላ ለኔ ጌታዬ
አመሠግናለሁ ስለጥበቃህ አመሠግናለሁ ስለእርዳታህ2X
ሳላውቅ ሳልሰማ ሳላይ ሳላውቅ ሳልሰማ ሳላይ
ስንት ጊዜ አዳንከኝ ከጠላቶቼ ቀስት ታደከኝ
ስንት ጊዜ አዳንከኝ ወጥመድን በመስበር ረዳኸኝ
ስላላየሁት ምህረት ስላላየሁት ጥበቃ ሳለላየሁት እርዳታ ክበር የኔ ጌታ ፡፡ 2X
በሰላም ወጥቼ በሰላም ገባለሁ
በአንተ ጥበቃ ይኸው ዛሬም አለሁ ይኸው ዛሬም አለሁ
በዙሪያ ቅጥርን አምላኬ ቀጥረሃል
በድካሜ ሁሉ ረዳት ሆነኸኛል ረዳት ሆነኸኛል፡፡
ቅጥር ነህ ለኔ ጋሻ ነህ ለኔ ከለላ ለኔ ጌታዬ
አመሠግናለሁ ስለጥበቃህ አመሠግናለሁ ስለእርዳታህ2X
በመንገዴ ሁሉ ሰላም እሄዳለሁ
አንተን ተማምኜ ሳልሰጋ ኖራለሁ ሳልሰጋ ኖራለሁ
ዙሪያ የሚሆኑ መላእክትን አዘሀል
በቀኝ በግራዬ ጠላቴ ይወድቃል ጠላቴ ይወድቃል፡፡
ቅጥር ነህ ለኔ ጋሻ ነህ ለኔ ከለላ ለኔ ጌታዬ
አመሠግናለሁ ስለጥበቃህ አመሠግናለሁ ስለእርዳታህ2X