አባል:Keti Jesus

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ሰው

ሰው በሀይሉ ብዛት

ደግሞ ቢደገፍ

ሰው በራሱ እውቀት

ደግሞ ቢመካ

ሰው በራሱ ክብር

ደግሞ ቢኩራራ

ሰው በራሱ ብርታት

ደግሞም ቢታመን


ምንኛ ምስኪን ነው

አንድ ቀን ጠፊ ነው (2x)

የእርሱ መታመኛው

ከንቱ ሞኝነት ነው


ግን ሰው በጌታ ቢታመን

ግን ሰው በእግዚአብሔር በኩራራ

ግን ሰው በጌታ ቢታመን

ግን ሰው በእግዚአብሔር ቢደገፍ


ዘላለም ነዋሪ ነው

የእርሱ መታመኛ ጋሻው ነዋሪ ነዉ (2x)


እኔ ግን መረጥኩኝ ይሻለኛል አልኩኝ በጌታ ታመንኩኝ

የእራሴ እውቀት ጥበብ አይጠቅመኝም አልኩኝ


እኔ ግን መረጥኩኝ ያዋጣኛል አልኩኝ (2x)

በጌታ ታመንኩኝ አይጥለኝም አልኩኝ


እግዚአብሔርን መፍራት

ከክፉ ሁሉ መራቅ

በእግዚአብሔር መታመን

እርሱን ብቻ ማክበር

እግዚአብሔር ማክበር

ፍቃድን መተግበር

ከአለም ሁሉ እድፍ

እራስን መሰወር


ይሄ መታደል ነው

ጠቢብም መሆን ነው 2x

የእግዚአብሔርን ፍቃድ

በህይወት መኖር ነው /በህይወት መግለጥ ነው