አባል:DawitMirkano

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን…..

ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ አምልኮ የሚገባውን እግዚአብሔርን አመልካለሁ ክብር የሚገባውን እግዚአብሔርን አከብራለሁ ዝማሬ የሚገባውን እግዚአብሔርን አደንቃለሁ

በህይወቴ ሳለሁ ለክብሩ እቀኛለሁ በምኖርበትም ዘመን እዘምራለሁ ደስ አሰኝቶኛል ቃሌ ለእርሱ ይጣፍጠው 2 ከፍ ብሎ ይክበር ውዳሴ የእርሱ ነው

ይኽው ይኽው ክብር ሁሉ የእርሱ ነው/4


እስቲ ላመስግነው ልቁም ስሙን ልጥራ ድንቁን ታአምራቱን ስራውንም ላውራ ክብሩን ልፈልገው ወደ ፊቱ ልግባ ከእግሩ ስር ልገኝ ምስጋናን ስሰዋ /2

ይኽው……


ታላቅ ምህረቱን ጽድቁን እቀኛለሁ ንጹህ መንገዱንም አስተውለዋለሁ በፍጥረት ሁሉ ላይ ከፍ ብሎ ልቋል ሁሉንም ሊገዛ በምድር ላይ ነግሷል /ከብሯል /2

ይኽው……


ሃሌ ሃሌሉያ ሃሌሉያ እያልኩኝ በቅኖቹ ሸንጐ በጉባኤ አለሁኝ ከጸሐይም መውጫ እስከ መግቢያው ድረስ ከህዝቡ ጋር እላለሁ ይሁን ስሙ ብሩክ /2

ይኽው……


ሰማያትን በብልሀት ምድርን በውሃ ላይ የሰራና ያጸና ያደረገ ከላይ ጠላትን በጥልቁ በባህር የጣለ ይኼ ነው ኢየሱስ እኛን የታደገ /ያሻገረ /2

ምስጋና …….

ይኽው……