ሳሙኤል ፡ ተገኝ (ሳሙኤል ፡ ተገኝ)
አውቀዋለሁ ጠረንህን መአዛህ ይለያል ጌታ
እሱን ሳገኝ እረሳለሁ ምድር ላይ መኖረንም ለ አፍታ
.
እንደማይወጡበት እንደ ጠሊቅ ባህር
ናፈቀኝ ካንተ ጋር በ መንፈስ መሰወር
.
አውቀዋለሁ......
1. ምንም የማይሞላው የህወቴ ጉድለት ክፍተቱ የማይታየኝ ዉሎየም አዳሬም ካንተ ጋ ሲሆን ነዉ ጠላቴ የማያገኘኝ አይኔ እምባ እያነባ በሃዘን መጥቼ በደስታ የሚመለሰው የ ነፍሴን በረሃ ማን አለ ካንተ ወጪ አርክቶ ሚያረሰርሰው
........አውቀዋለሁ......
2. የፈራሁት ነገር ይወርሰኛል ያልኩት ስትመጣ ወዲያው አጣሁት የከበደኝ ሁሉ ሸክም የሆነብኝ ስትመጣ ወዲያው ቀልለኝ የሌሊቱ ግርማ የህወቴ ፅልመት ሊወስደኝ ሲጥር ወደ ሞተ ድል ያስለመደኝ መንፈስ ቅዱስ መጣ የንጋቴ ፀሐይ ወጣ
አውቀዋለሁ........
ያንተ መኖር መኖሬን ይወስናል ይሄ ነዉ የህወት ስሌቱ ያለዚያማ መኖር ትርጉም የለው ራስን ማሰንበት ለከንቱ... . እረፍት አልሰጣቸው ለ አይኖቼ ሽፋሽፍት እስኪያዩ የ አንተን መገኘት ጉልበቴም እስኪዝል ይምበርከክ ደጅ ይጥና ናፍቆቱ አንተ ነህና
ፍስሃዬ ደስታዬ አለኝታዬ መከታዬ ነህአንተ ካለህልኝ ሁሉ እንዳለኝ ይሰማኛል ምንም እንዳልጎደለ . አውቀዋለሁ ጠረንህን....