ማራናታ በረከት ተስፋዬ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የመምጣትህ ፡ ነገር ፡ የመጨረሻው
የነገርከን ፡ ትንቢት ፡ እየሆነ፡ ነው
ናፍቆቱ ፡ አስባለኝ ፡ አሜን ፡ ማራናታ
ላይህ ፡ ጓጉቻለው ፡ ኢየሱስ ፡ የኔ ፡ ጌታ


ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አትመጣም ፡ ወይ
የደማልኝን ፡ ጎንህን ፡ ልይ
አንተን ፡ ለማየት ፡ ዓይኖቼ ፡ ሻቱ
ቶሎ ፡ ናልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ የናዝሬቱ


ካንተ ፡ ጋር ፡ ልዋል ፡ ካንተ ፡ ጋር ፡ ልደር
እንደ ፡ ዩሐንስ ፡ በደረትህ ፡ ሥር
ደስታዬ ፡ የምለው ፡ ትልቁ ፡ እርካታዬ
አንተ ፡ ያለህበት ፡ ስኖር  ፡ ነዉ ፡ ጌታዬ
በሌለህበት ፡ ከማገኝ ፡ ድሎት
ምድረበዳ ፡ ላይ ፡ ካንተ ፡ ጋር ፡ ልሰንብት
አንተን ፡ የማየት ፡ ናፍቆት ፡ ገባብኝ
እንደ  ፡ ጓጓሁኝ ፡ መች ፡ እቀራለሁኝ


ከአመፃ ፡ ብዛት ፡ ፍቅር  ፡ ቀዘቀዘ
ሰው ፡ ወንድሙን ፡ ገሎ ፡ መቼ ፡ ተወቀሰ
አመፀኞች ፡ በዙ ፡ ክፋቱ ፡ ጨምሮ
ተላልፈው ፡ ተሰጡ ፡ ለማይረባ ፡ አዕምሮ


የድሆች ፡ ዳኛ ፡ የሁሉ ፡ አለቃ
ና፡ እና ፡ ከልክለዉ ፡ ለቅሶአችን ፡ ይብቃ
የእናቶች ፡ እንባ ፡ ይላል ፡ ዋይ ፡ ዋይ
ሩህሩህ ፡ ጌታ ፡ አትመጣም ፡ ወይ

    ቤተ ክርስቲያን ፡ ተነሺ ፡ እና ፡ አብሪ
ፍቅርን ፡ ለጣሉ ፡ እንዳትዘምሪ
የገሃነም ፡ ደጅ ፡ ለካ ፡ ጥላቻ ፡ ነው
ማይቋቋምሽ ፡ ሰይፍሽ ፡ ፍቅር ፡ ሲሆን ፡ ነው
ጦር ፡ መሳርያውን ፡ ፍቅር ፡ ያደረገ
ጠላቱን ፡ ረቶ ፡ ወንድም ፡ አደረገ
የሰው ፡ ጠባብ ፡ አፍ ፡ የሚጎርስ ፡ እህል
ክፉ ፡ አንደበት ፡ አክሏል ፡ ሲዖል


አትመጣም ፡ ወይ
ማራናታ
አናርፍም ፡ ወይ
ማራናታ (፪x)

ናናናና
ማራናታ 4x


ሃሳዊ ፡ መምህራን ፡ ነብያቶች ፡ በዙ
ተናገረኝ ፡ ባዮች ፡ ለገንዘብ ፡ የተገዙ
ለታመመዉ ፡ ምስኪን ፡ እንግዳ ፡ ማረፊያ
በሽታው ፡ ሳያንሰዉ ፡ በፀሎት ፡ ሰበብ ፡ዝርፊያ


ደምህ ፡ ተረግጦ ፡ ገንዘብ ፡ ገነነ
አንተን ፡ ያወቀ ፡ ሰው ፡ ክፉ ፡ ሆነ
ነዋይ ፡ ሚያፈቅር ፡ ትውልድ ፡ ተነሳ
ያረክለትን ፡ ምህረት ፡ የረሳ


ፈዉሱ ፡ ለታይታ ፡ ለንግድ ፡ ቀረበ
በአዳኙ ፡ ስም ፡ ገንዘብ ፡ ተሰበሰበ
ገበያው ፡ ደርቶ ፡ በወንጌል ፡ ሰበብ
ስንቱን ፡ ታዘብነው ፡ አወይ ፡ ጉድ ፡ አጀብ
በሰጠዉ ፡ ፀጋ ፡ የሆነ ፡ ነጋዴ
በፍርድ ፡ ቀን ፡ የሚል ፡ ነው ፡ ወይኔ ፡ ጉዴ
መምጣቱ ፡ አይቀርም ፡ የእረኞች ፡ አለቃ
ስለበጎቹ ፡ የሚራራ ፡ ጠንቃቃ


አትመጣም ፡ ወይ
ማራናታ
አናርፍም ፡ ወይ
ማራናታ (፪x)

ናናናና
ማራናታ (፬x)


ወደ ፡ ዓለም ፡ ሂድ ፡ ወንጌልን ፡ ስበኩ
ነበር ፡ የተባልነው ፡ መስክሩ ፡ ታደጉ
ሰው ፡ ግን ፡ ካስማ ፡ ሰርቶ ፡ ወንበሯን ፡ ወደደ
መምህርና ፡ እና፡ ጌታ ፡ መባልን ፡ ለመደ

     ወንጌል ፡ እንስራ ፡ አንቱታው ፡ ቀርቶ
ይሸለም ፡ የለ ፡ ወይ ፡ የሰራ ፡ ተግቶ
ከታበይንበት ፡ ዙፋናችን
እስኪ ፡ እንውረድ ፡ ለጌታችን


አላወጣንም ፡ አጋንንቶችን
አልፈወስንም ፡ ወይ ፡ በሽተኞችን
ጌታ ፡ በስምህ ፡ ብዙ ፡ አድርገን
አላዉቃችሁም ፡ ስለምን ፡ አልከን
ከሚሉት ፡ ወገን ፡ እንዳይሆን ፡ ህይወቴ
መብራቴን ፡ ላብራ ፡ ሳይጎድል ፡ ዘይቴ
እስክትመጣልኝ ፡ ወይ ፡ እስክትወስደኝ
እየጠበኩክ ፡ እፀናለሁኝ


ናናናና
ማራናታ (፬x)