መስቀልህን አያለሁ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዓይኖቼን ከመስቀልህ አንስቼ

ወዴት እሄዳለሁ ካንተ ርቄ (2)

የሕይወቴ ሰላም ሁሌ የሚፈልቅበት

ከጭንቀትም ሁሉ ልቤ የሚያርፍበት

ሐዘን ከኔ ርቆ ደስታን የማገኘው ዓይኖቼን አንስቼ መስቀልህን ሳይ ነው

ዓይኔን የጣልኩበት ከመስቀልህ ሌላ ዘለቄታ የሌለው ጠፊ ነው በኋላ ዓለሙም ምኞቱም ሁሉም ያልፋልና

እርዳኝ የኔ ጌታ ባንተ እንድፀና

ዓይኖቼን ከመስቀልህ...

የሚያስጨንቀኝን ላንተው እነግራለሁ ትካዜዬን ሁሉ ባንተ ላይ እጥላለሁ የመድሐኒቴ አምላክ ተስፋ አደርግሀለሁ/2/

ሰላም እረፍት መታደስን የማገኝበት ስብራቴም የሚጠገንበት አይኖቼን ወዳንተ አነሳለሁ መስቀልህን አያለሁ

ወዴት እሄዳለሁ ካንተ ርቄ