ልናርፍ ነው

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ: ልናርፍ ነው ወንድም/እህት ልናርፍ ነው እየሱስ ሊመጣ ሊወስደን ነው።

መለከት ሊነፋ መላዕክቱን ሊያዝ ነው የልጆቹ ነገር አላስችል እያለው ጌታችን ይመጣል ከጽዮን ተራራ ልንሄድ ነው እኛም ልንኖር ከርሱ ጋራ።

አዝ: ልናርፍ ነው ወንድም/እህት ልናርፍ ነው እየሱስ ሊመጣ ሊወስደን ነው።

መሯሯጥ መባከን ይሄ ሁሉ ይቀራል የሚያስፈልገንን የሱስ አዘጋጅቷል ዓይናችን ተከፍቶ ጌታን ልናየው ነው እጆቹን ዘርግቶ እኛን ሊቀበል ነው።

አዝ: ልናርፍ ነው ወንድም/እህት ልናርፍ ነው እየሱስ ሊመጣ ሊወስደን ነው።

እንበርታ እንጽና ዕንባችን እንዋጠው ተስፋችን ሊመጣ ሊያሳርፈን ነው የሱስ ሊመጣ ነው ከመላዕክት ጋራ ልናርፍ ነው እኛም ከዚህ ዓለም መከራ

ልናርፍ ነው ወንድም/እህት ልናርፍ ነው እየሱስ ሊመጣ ሊወስደን ነው