ሄለን እምሩ (ሄሊ)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ



ማነው ያልታሰብ ያልተረዳ ባንተ ዝም ብለህ ያለፍከው ጨልሞበት አይተህ ማነው ያልመክርከው ያልሆንክልት አባት ክማበል አምልጦ ያልዳነ ከእሳት

          ሰምቼ ነብረ ፍቅር ነህ እያሉ
          በቃላት ሊገልጡህ ሲያንሱ ሲጥሉ
          በኔ ደርሶ አየሁት በልጦ ከሰማሁት
         የፍቅር ልብህን ክልቤ ወደድኩት

ማን አለ ያዘነ አድርገኸው ባዳ ሁሉን ትቶ መጥቶ ባንተ የተጎዳ ማን ሆን ባይተዋር አንተን ብሎ መቶ ቆሞ መሄድ ቻል ከፍቅርህ ጠጥቶ

      ዳካማው ታስቦ ፅኑ ሐያል ተባል
       ተባብረው የጣሉት ባንተ ክብር አየ
       ያሳደደህን ሰው መቼ ተባቀልከው
      ይልቅ ሰው አድርገህ ስንቱን አከበርከው

ሰው ሁሉ የረሳው ፊቱን ያዞረብት ባንተ አይደለም ወይ እንዲህ ያማረብት ስንቱን ራራህለት ስንቱን አባት ሆንከው ዘመድ የለኝ ላለው ስንቱን ተዛመድከው

           ኢየሱስ የሚባል አንድ ወዳጅ አለኝ
           ሰው በራቀኝ ጊዜ እየቀረበኝ
           አይዞሽ ልጄ ሆይ እኔ አለሁ እያለኝ
            ሰብስቦ የያዛኝ አባት የሆነኝ

ክቤት ወዲት እሄዳልሁ ዘላለም ቤቴ ባንተ እጅ ነው ስለዚህ ጌታ አንተው ምራኝ ከጆችህ ምንም አይለየኝ አንተ ነህ የእኔ እረኛ አንተ ነህ የማትተኛ አንተ ነህ የኔ መሪዬ አንተ ነህ ከሞት ያዳንከኝ