From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ አልቅበዘበዝም ፡ ከእንግዲህማ
በሥጋ ፡ አልወጣም ፡ ከእንግዲህማ
ግን ፡ በቃልህ ፡ መረቤን/ነገሬን ፡ እጥላለሁ
የተሻለ ፡ ያን ፡ ጊዜ ፡ አገኛለሁ (፪x)
እንደ ፡ ቃልህ ፡ መረቤን ፡ እጥላለሁ
የተሻለ ፡ በቃልህ/በጌታ ፡ አገኛለሁ (፪x)
የድካም ፡ ሌሊት ፡ ሆኖ ፡ ሌሊቱ
ለካ ፡ ይፈተናል ፡ ሰውም ፡ ትዕግሥቱ
የራሴን ፡ ጥረት ፡ ሁሉ ፡ ጥሬያለሁ
ታንኳ ፡ መረቤ ፡ ባየው ፡ ባዶ ፡ ነው
አሁንማ ፡ በቃልህ ፡ መረቤን ፡ እጥላለሁ
አሁንም ፡ ሙግቴን ፡ ሁሉ ፡ እተዋለሁ
አሁንማ ፡ የአንተ ፡ ሃሳብ ፡ ይሻላል ፡ እላለሁ
አሁንማ ፡ አየሁት ፡ የእኔማ ፡ ከንቱ ፡ ነው
መቼ ፡ ከጉድጓድ ፡ ጋር ፡ የይሳቅ ፡ ነገሩ
የአምላኩ ፡ ቃልኪዳን ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ መኖሩ
በስጥና ፡ በኤሴቅ ፡ ሲያጋፉት ፡ ቢያያቸው
ርሆቦት ፡ ደረሰ ፡ ሁሉን ፡ ትቶላቸው
በረከቴ ፡ ብለው ፡ ጉድጓዱን ፡ ለሚያዩ
አይደለም ፡ አልኳቸው ፡ ከላይ ፡ ነው ፡ ጉዳዩ
ሰው ፡ ቆፍሮ ፡ ያመጣው ፡ ይነቅፋል ፡ ይደርቃል
በቃልህ ፡ የጀመረ ፡ እርሱ ፡ መቼ ፡ ያፍራል
አዝ፦ አልቅበዘበዝም ፡ ከእንግዲህማ
በሥጋ ፡ አልወጣም ፡ ከእንግዲህማ
ግን ፡ በቃልህ ፡ መረቤን/ነገሬን ፡ እጥላለሁ
የተሻለ ፡ ያን ፡ ጊዜ ፡ አገኛለሁ (፪x)
እንደ ፡ ቃልህ ፡ መረቤን ፡ እጥላለሁ
የተሻለ ፡ በቃልህ/በጌታ ፡ አገኛለሁ (፪x)
ስለ ፡ እኔ ፡ አውቃለሁ ፡ ሃሳቢ ፡ አልሻም
ውጥኔ ፡ በእጄ ፡ አለው ፡ መድረሻ
ብዬ ፡ ፎክሬ ፡ በራሴ ፡ ትግል
ኋላ ፡ ነቃሁኝ ፡ ስደክም ፡ ስዝል
አሁንማ ፡ ፈቃድህ ፡ ይሆን ፡ እላለሁ
አሁንማ ፡ ከአንተ ፡ የሆነውን ፡ እሻለሁ
አሁንማ ፡ . (1) . ፡ መስገን ፡ እንዳይሆን ፡ እጣዬ
አሁንማ ፡ እንደቃልህ ፡ መረብ ፡ ኑሮዬ
አዝ፦ አልቅበዘበዝም ፡ ከእንግዲህማ
በሥጋ ፡ አልወጣም ፡ ከእንግዲህማ
ግን ፡ በቃልህ ፡ መረቤን/ነገሬን ፡ እጥላለሁ
የተሻለ ፡ ያን ፡ ጊዜ ፡ አገኛለሁ (፪x)
መቼ ፡ ከጉድጓድ ፡ ጋር ፡ የይሳቅ ፡ ነገሩ
የአምላኩ ፡ ቃልኪዳን ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ መኖሩ
በስጥና ፡ በኤሴቅ ፡ ሲያጋፉት ፡ ቢያያቸው
ርሆቦት ፡ ደረሰ ፡ ሁሉን ፡ ትቶላቸው
በረከቴ ፡ ብለው ፡ ጉድጓዱን ፡ ለሚያዩ
አይደለም ፡ አልኳቸው ፡ ከላይ ፡ ነው ፡ ጉዳዩ
ሰው ፡ ቆፍሮ ፡ ያመጣው ፡ ይነቅፋል ፡ ይደርቃል
በቃልህ ፡ የጀመረ ፡ እርሱ ፡ መቼ ፡ ያፍራል
|