የሚያጽናናኝ (Yemiyatsenanagn) - አገኘሁ ፡ ይደግ ፡ እና ፡ እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
Broom.png ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት
አገኘሁ ፡ ይደግ ፡ እና ፡ እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Agegnehu Yideg and Endale Woldegiorgis)

Lyrics.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

የድል ፡ ዘመን
(Yedil Zemen)

ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአገኘሁ ፡ ይደግ ፡ እና ፡ እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Agegnehu Yideg and Endale Woldegiorgis)

የሚያጽናናኝ ልቤን ሚደግፈው /2
ብቻዬን አይደለሁም አብ ከኔ ጋራ ነው
ብቻዬን አይደለሁም ጌታ ከኔ ጋራ ነው //2//

የሰው አብሮነት የሰው አጄብታ
ድንገት ያቆማል ሲመጣ ማታ
ሁሉም ሲገባ ወደየቤቱ
አለሁኝ የሚል በምህረቱ
ለብቻዬ የማይተወኝ
አብ ሁልጊዜ ጎኔ አለልኝ //2//

አቅፎ ሳሚ መሳይ ወዳጅ
በቁም ሚቀብር ገዳይ ነጋጅ
አለሁ ብሎ ሄዶ ሚሸጥ
አሳልፎ ለሞት ሚሰጥ
ይሁዳዬን አይቻለሁ
ተከዳሁ ስል አምብቻለሁ
ግን ተጽናናሁ በረታሁ
ከሃዘን ወንበር ተነሳሁ
ለብቻዬ የማይተወኝ
አብ ሁልጊዜ ጎኔ አለልኝ //2//

አባ አባባ /3
አብ አለኝ ፍፁም ማይተወኝ
የሚያጽናናኝ ልቤን ሚደግፈው
ብቻዬን አይደለሁም አብ ከእኔ ጋራ ነው
ብቻዬን አይደለሁም ጌታ ከእኔ ጋራ ነው //2