መድኃኒቴን ፡ አየዋለው (Medhanitien Ayewalew) - አብርሃም ፡ እና ፡ እያሱ ፡ ተክለማሪያም

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አብርሃም ፡ እና ፡ እያሱ ፡ ተክለማሪያም
(Abraham and Eyasu Teklemariam)

Abraham and Eyasu Teklemariam 2.jpg


(2)

ዘመናት ፡ አይለውጡህም
(Zemenat Aylewetuhem)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 6:07
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአብርሃም ፡ እና ፡ እያሱ ፡ ተክለማሪያም ፡ አልበሞች
(Albums by Abraham and Eyasu Teklemariam)

መድኃኒቴን ፡ አየዋለሁ ፡ ዓይኖቼ ፡ ተከፍተዋል
በደሙና ፡ በስሙ ፡ ስላነጻን
ፍፁም ፡ ህይወት ፡ አሁን ፡ አለኝ ፡ በሞቱ ፡ ፈወሰኝ
አሮጌው ፡ ልማድ ፡ ከሕይወቴ ፡ ጠፍቷል

አዝ:- አምላኬን ፡ ላመስግን ፡ ሥሙንም ፡ ልወድስ
ስላፈቀረኝ ፡ በመስቀል ፡ ተሰቅሎ (ሃሌሉያ)
በሕይወቴ ፡ ዘመን ፡ ሁሉ ፡ ኢየሱሴን ፡ ልወድስ
ለዓለም ፡ ህዝቦች ፡ የፍቅሩን ፡ ወንጌል ፡ ልግለጽ (፪x)

ትኩስ ፡ ቀዝቃዛ ፡ ለብ ፡ ያለ ፡ ህይወት ፡ አትመኑ
የጌታ ፡ አገልጋይ ፡ እሳት ፡ ነበልባል ፡ ነው
በመንፈስ ፡ እሳት ፡ ግላቹህ ፡ እርሱን ፡ አገልግሉ
የድሉን ፡ አክሊል ፡ እንድትቀበሉ
 
አዝ:- ፡ አምላኬን ፡ ላመስግን ፡ ሥሙንም ፡ ልወድስ
ስላፈቀረኝ ፡ በመስቀል ፡ ተሰቅሎ (ሃሌሉያ)
በሕይወቴ ፡ ዘመን ፡ ሁሉ ፡ ኢየሱሴን ፡ ልወድስ
ለዓለም ፡ ህዝቦች ፡ የፍቅሩን ፡ ወንጌል ፡ ልግለጽ (፪x)

ነፍሴ ፡ አርፋለች ፡ በዙፋንህ ፡ ሥር
በጥላህ ፡ እታመናለሁ
መፍትሄ ፡ የሌለው ፡ ምንም ፡ ችግር
እንደማያገኘኝ ፡ አውቃለሁ

ከአንተ ፡ የተሻለ ፡ ጓደኛ ፡ የለኝም
ከአንተ ፡ የቀረበ ፡ ዘመድ ፡ አላገኝም
ከአንተ ፡ የበለጠ ፡ ምንም ፡ አልመኝም
ሆሆሆ ፡ ኢየሱስ ፡ አለልኝ ፡ ምንም ፡ አይጐለኝም (፫x)