From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
አባ. ናትናኤል ፡ ታየ (Abba. Natnael Taye)
|
|
()
|
ማን ፡ ብዬ ፡ ልጥራ ፡ ስምህን (Man Beyie Letra Semehen)
|
ቁጥር (Track):
|
፪ (2)
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የአባ. ናትናኤል ፡ ታየ ፡ አልበሞች (Albums by Abba. Natnael Taye)
|
|
በአፍላ ፡ ልጅነት ፡ እራዕይ ፡ ሰጥቶኝ
ውስጤ ፡ እይፈላ ፡ እንዴት ፡ ያስችለኝ
በዚህ ፡ ደስ ፡ ብሎኝ ፡ ብሰብክ ፡ ባወራ
መንገድ ፡ ዘጋብኝ ፡ ያባላጋራ
በአጭር ፡ ቀጨሁት ፡ ብሎ ፡ ሲዝናና
ጥሼው ፡ መሄዴን ፡ አላየምና
ተጥዬ ፡ የምቀር ፡ መስሎታልና
እንዲህ ፡ የዋዛ ፡ መቼ ፡ ሆንኩና
መስሎት ፡ የፈራሁ ፡ ገና ፡ ለገና
ጉዱ ፡ ፈላበት ፡ ነካካኝና
አዝ፦ ወረደ ፡ አምላኬ ፡ ከሃያላን ፡ ጋራ
ከሰማይ ፡ መቅደሱ ፡ አያበራ
ወረደ ፡ አምላኬ ፡ ከሃያላኑ ፡ ጋር
በሰልፉ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ሊዋጋ
አልመለስም ፡ ሰልፉን ፡ ፈርቼ ፤ አልመለስም ፡ ቅባቱን ፡ ይዤ
አልመለሰም ፡ አምላኬን ፡ ይዤ ፣ አልመለስም ፡ ቅባቱን ፡ ይዤ
አልመለስም ፡ ሰልፉን ፡ ፈርቼ ፤ አልመለስም ፡ ቅባቱን ፡ ይዤ
ምንም ፡ ቢያወራ ፡ እኔ ፡ ላልፈራ
አታመልጠኝም ፡ ቢል ፡ ለፉከራ
ዛቻ ፡ ፉከራ ፡ ላይሆን ፡ ላይሰራ
ጸጉሬን ፡ ዐይነካም ፡ ምን ፡ ቢንጠራራ
ዝምበል ፡ ጠላቴ ፡ እስኪ ፡ አትፎክር
ከአንተ ፡ የሚበልጥ ፡ አለኝ ፡ እግዚአብሔር
ሰልፉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ መሆኑን ፡ ሳያውቅ
ዘሎ ፡ ገባበት ፡ አቤት ፡ መናናቅ
ወይ ፡ አለማሰብ ፡ አዬ ፡ መሳሳት
መቼ ፡ ይሆናል ፡ በእሳት ፡ መጫወት
አዝ፦ ወረደ ፡ አምላኬ ፡ ከሃያላን ፡ ጋራ
ከሰማይ ፡ መቅደሱ ፡ አያበራ
ወረደ ፡ አምላኬ ፡ ከሃያላኑ ፡ ጋር
በሰልፉ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ሊዋጋ
አልመለስም ፡ ሰልፉን ፡ ፈርቼ ፤ አልመለስም ፡ ቅባቱን ፡ ይዤ
አልመለሰም ፡ አምላኬን ፡ ይዤ ፣ አልመለስም ፡ ቅባቱን ፡ ይዤ
አልመለስም ፡ ሰልፉን ፡ ፈርቼ ፤ አልመለስም ፡ ቅባቱን ፡ ይዤ
ጠላቴ ፡ ሲያየኝ ፡ መስሎት ፡ ማልበቃ
ጌታ ፡ ግን ፡ ቀባኝ ፡ አድርጐ ፡ አለቃ
ሰው ፡ ሁሉ ፡ ሲያየኝ ፡ አንተ ፡ ብላቴና
አትችለውም ፡ ህጻን ፡ ነህና
ህጻን ፡ ብመስልም ፡ ምንም ፡ ማልረባ
ገልብጬው ፡ መጣሁ ፡ ያንን ፡ ገለባ
ሲያስብ ፡ ጠላቴ ፡ በአምላኬ ፡ ማፍር
እኔ ፡ ሳለቅስ ፡ እርሱ ፡ ሊፎክር
ተአምር ፡ ሰራና ፡ የእኔ ፡ እግዚአብሔር
ከዐይኔ ፡ አስወገደው ፡ እስኪ ፡ ልዘምር