From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
አባ. ናትናኤል ፡ ታየ (Abba. Natnael Taye)
|
|
(Volume)
|
ማን ፡ ብዬ ፡ ልጥራ ፡ ስምህን (Man Beyie Letra Semehen)
|
ቁጥር (Track):
|
፫ (3)
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የአባ. ናትናኤል ፡ ታየ ፡ አልበሞች (Albums by Abba. Natnael Taye)
|
|
አዝ፦ በንሰሃ ፡ ለመመለስ
ወደ ፡ ዙፋንህ ፡ ለመድረስ
መጥተናል ፡ ተቀበለን
በደላችንን ፡ ይቅር ፡ በለን (፪x)
የቤትህን ፡ ተድላን ፡ ሰላም ፡ ተቀምተን
ከፍ ፡ ካድረከን ፡ ከጉያህ ፡ ውስጥ ፡ ወተን
ጠላትህ ፡ ረጋግጦ ፡ ብዙ ፡ አጐሳቁሎናል
በምህረትህ ፡ ጐብኘን ፡ ፊትህ ፡ ይሻለናል
የዓለምን ፡ ምርኩዝ ፡ ኀጢአት ፡ ተደግፈን
በስራ ፡ ሳንለይ ፡ እንዲሁን ፡ በአፋችን
አሁን ፡ ምኑ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ የእኛ ፡ ሕይወታችን
በጌታ ፡ ቤት ፡ ሆነን ፡ እየተገፋፋን
አዝ፦ በንሰሃ ፡ ለመመለስ
ወደ ፡ ዙፋንህ ፡ ለመድረስ
መጥተናል ፡ ተቀበለን
በደላችንን ፡ ይቅር ፡ በለን (፪x)
ይብቃን ፡ አሁን ፡ ይብቃን ፡ እንደሬት ፡ ይምረረን
ኀጢአትን ፡ እንጥላው ፡ በንሰሃ ፡ ታጥበን
እንደጌታ ፡ ያለ ፡ የትም ፡ አናገኝም
አይተነው ፡ የለም ፡ ወይ ፡ ቆሻሻውን ፡ ዓለም
በስም ፡ ክርስትና ፡ ብለን ፡ ተሸፍነን
በቃላት ፡ ታጅበን ፡ ለሚያየን ፡ ሰው ፡ መስለን
ምንም ፡ አልተለወጥን ፡ ገባ ፡ ብሎ ፡ ለአየን
ሌላ ፡ ስም ፡ የለንም ፡ ይህ ፡ ነው ፡ ታሪካችን
አዝ፦ በንሰሃ ፡ ለመመለስ
ወደ ፡ ዙፋንህ ፡ ለመድረስ
መጥተናል ፡ ተቀበለን
በደላችንን ፡ ይቅር ፡ በለን (፪x)
"እንደ ፡ ምህረትህ ፡ ብዛት
እንደቸርነትህ ፡ መጠን
ለአምጻችንና ፡ ለኀጢአታችን ፡ ፍሬ
አሳልፈህ ፡ አትስጠን"
ዘር ፡ ቀለምን ፡ ለየን ፡ የእኛ ፡ ጉድ ፡ አያልቅም
አንድ ፡ ያደረከንን ፡ ጌታ ፡ ለዘለዓለም
ዐይናችን ፡ ጨልሞ ፡ ከፋፍለን ፡ ብናይም
ባሪያ ፡ ጨዋ ፡ ብሎ ፡ ቃሉ ፡ አይለያየንም
ክርስቶሥን ፡ ለብሶ ፡ አይሁድ ፡ ግሪክ ፡ የለም
የጸና ፡ ቃል ፡ አለን ፡ ማንም ፡ አይሽረውም
እንመለስ ፡ አሁን ፡ ጌታ ፡ መሃሪ ፡ ነው
እርሱ ፡ ይቅር ፡ ሊለን ፡ ሁሌም ፡ ዝግጁ ፡ ነው
አዝ፦ በንሰሃ ፡ ለመመለስ
ወደ ፡ ዙፋንህ ፡ ለመድረስ
መጥተናል ፡ ተቀበለን
በደላችንን ፡ ይቅር ፡ በለን (፪x)
አጣፍጠን ፡ ብንዘምር ፡ አንደበትን ፡ ስለን
ጌታ ፡ ሚፈልገው ፡ መቀደሳችንን
ድምጹን ፡ እናዳምጠው ፡ እስኪ ፡ እንተላለፍ
በስራ ፡ እንለይ ፡ በቃል ፡ ከመለፍለፍ
የድፍረት ፡ ኀጢአት ፡ አናፍርም ፡ ስንሰራ
እንደ ፡ ኤሊ ፡ ልጆች ፡ በነውር ፡ ስንኮራ
ምክር ፡ ግሳጼንም ፡ እንሰማም ፡ ብለናል
በመስዋዕቱ ፡ ሥጋ ፡ ልባችን ፡ ደንድኗል
አዝ፦ በንሰሃ ፡ ለመመለስ
ወደ ፡ ዙፋንህ ፡ ለመድረስ
መጥተናል ፡ ተቀበለን
በደላችንን ፡ ይቅር ፡ በለን (፪x)
|