ከሰማያት ፡ በላይ (Belay) - ዮሐንስ ፡ ግርማ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዮሐንስ ፡ ግርማ
(Yohannes Girma)

Yohannes Girma 2.jpg


(2)

እርስቴ ፡ ነህ
(Erestie Neh)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 4:49
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሐንስ ፡ ግርማ ፡ አልበሞች
(Albums by Yohannes Girma)

ሠማይን ዘርግተህ እንዲህ አንጣለሃል
ከትልቅነቱ ብዛት የሰው ስሌት ያልፋል
አንተ የሰራኸው
በስንዝር የለካኸው
ይህ ሰማይ ትልቅ ከተባለ
አንተ ምን ትባላለህ

አዝ፦ ከሰማያት በላይ በላይ
ከምድርም በላይ በላይ
ከፍጥረታት በላይ በላይ
አንት ትልቅ ነህ
አንት ትልቅ ነህ (3x)

በምድር የሰው ቁጥር እጅጉን ብዙ ነው
ከአዳም ጀምሮ እስካሁን የኖረው
በፊት ይህ ሁሉ ሲታይ የእኔ ጌታ
በገንቦ እንዳለች ትንሽ ጠብታ
ምትገርም ነህ ጌታ

አዝ፦ ከሰማያት በላይ በላይ
ከምድርም በላይ በላይ
ከፍጥረታት በላይ በላይ
አንት ትልቅ ነህ
አንት ትልቅ ነህ (3x)

በምድር ለሚኖሩ ምድር ሰፊ እርስት ናት
ስፋቷን በብዙ ቁጥር የሚያሰሏት
አንተ ግን ጌታዬ ትልቅ ትልቅ ነህ
በክበቦቿ ላይ ትቀመጣለህ
ከፍ ከፍ ላድርግህ

አዝ፦ ከሰማያት በላይ በላይ
ከምድርም በላይ በላይ
ከፍጥረታት በላይ በላይ
አንት ትልቅ ነህ
አንት ትልቅ ነህ (5x)