እረኛዬ (Ereñayie) - ዮሐንስ ፡ ግርማ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዮሐንስ ፡ ግርማ
(Yohannes Girma)

Lyrics.jpg


(1)

አልበም
(Ereñayie)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 7:26
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሐንስ ፡ ግርማ ፡ አልበሞች
(Albums by Yohannes Girma)

እረኛዬ ማረፊያዬ
ቃልክን ስትናገር ልብን ያሳርፋል
የምትመክረው ምክር ተስፋን ያሳድራል
ሆነህ አይቼሀለሁ ልቤ አንተን ወዶሀል /x2

አይከፋኝም አባ ለዚህ አትስጋ
ምን ጎደለው አንተን የተጠጋ
መተማመን መጓደድ ባንተ ነው
ሁሉ ባለህ ሁሉን በፈጠርከው
አይኖችህ በምድር ላይ ያያሉ
ከእኔው ጋራ ይንከራተታሉ
ሆድ ሲብሰኝ ከላይ ትወርዳለህ
በደመናት ትረማመዳለህ

እረኛዬ...

ማይናወጥ ፀንቶ የሚኖረው
ሰላም ደስታ ነፍሴን ሚመግበው
መቼ በቁስ በመብል ወርቅ ሆነ
በሚጠፉ መቼ እንዲህ ታጀበ
ሲከናወን ቤት ጓዳ ሲሞላ
ኑሮ ሲተርፍ ለአፈር ሲደላ
አይደል በዚህ ደስታዬ ባንተ ነው
ጠፊ ነገር ሊያጠፋኝ አይከጅልም

እረኛዬ...

የገባከውን ቃል ኪዳን አትረሳም
የሰጠኸውን ተስፋ አታጠፋም
ሌት እና ቀን ሁሌ ትተጋለህ
እንዲፈፀም ቀኑን ታፈጥናለህ
ይህን ላደርግ ሀይሌ እንዲህ አነሰ
ብለህ አትመጣ ጉልበቴ ደከመ
ባንተው ምለህ መች እንዲህ ይሆናል
ችሎታህም ሁሌ ያስተማምናል

እረኛዬ...

ልቤ በሰው መቼም አይመካም
ምደገፈው ፈራሽ አልጠጋም
አይኑ በሰው በሟቹ ያረፈ
እሱ ሲሞት ተስፋውም አረፈ
ድንገት አርፈህ መርዶ አይነገር
መንግስት ከአንተ ለሌላ አይሻገር
በጉልበትህ ፅናት ትሄዳለህ
ለዘላለም ንጉስ ትባላለህ

እረኛዬ...