መቅበዝበዝ ፡ ሳበዛ (አንተን ያገኘሁ ዕለት) (Meqbezbez Sabeza) - ዮሐንስ ፡ ግርማ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዮሐንስ ፡ ግርማ
(Yohannes Girma)

Yohannes Girma 3.jpg


(3)

አምላኬ ፡ ደስታዬ
(Amlakie Destayie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 8፡02
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሐንስ ፡ ግርማ ፡ አልበሞች
(Albums by Yohannes Girma)

መቅበዝበዝ ሳበዛ በዓለም ስዋትት
ክብር መስሎኝ ታይቶኝ ውርደት ሳካብት
በበደሌ ብዛት ሞት የሚገባኝን
ፀጋህን አብዝተህ በህይወት ኖርኩኝ
ዛሬ ላንተ ቆሜ ባፌ ዘምራለሁ
ያዳንከውን አዳዳን ገድልህን አወራለሁ
ግነን በዓለማት ስምህ ከፍ ይበል
በእርግጥ ከዚህ በቀር የለም የምከፍልህ

አንተን ያገኘሁ ለት መንገዴ ተቃና
በእጆችህ መራኸኝ በህይወት ጎዳና
ምክርህ ሰው ያደርጋል የአንደበትህ ቃል
ፍቅርህ እንደ ጠል ነው ደረቁን ያፀድቃል (2)

ስንከራተት ሳለ በምድረበዳ ላይ
የሚረዳኝ የለም ግራ ቀኜን አላይ
ባልጠበኩት ለታ ከሰማይ ድምፅ መጣ
በእጁ እጄን ያዘኝ ተራራን አወጣኝ
አንተ የኔ እኮ ነህ ልጄ እወድሃለሁ
በእውነት ቃል አስቤህ ለክብር ወልጄሃለሁ
ለዘላለም ፍቅሬ ካንተ አትለይም
አለኝ ለዘለዓለም እኔ አልጥልህም

አንተን ያገኘሁ ለት (አዝ)

እርጥበት የማያውቅ በድርቅ የደቀቀ
ህይወቴ ነበረ ከአጥንት የደረቀ
ከፍጥረቴ ሳለሁ የበረሃ ወይራ
መጠጊያን አገኘሁ በመልካሙ ስፍራ
ኩሩው ሊያስቀና ምስኪኑን መረጠ
ከውድረደት አንስቶ ለክብር አስቀመጠ
በእርሱ ተተክዬ በመልካሙ ግንድ ስር
ልምላሜን አገኘሁ ለዘላለም ይክበር

አንተን ያገኘሁ ለት (አዝ)

ጠመዝማዛ ጉዞ ቁልቁለት ሳዘግም
ሞቴን ለማፋጠን ኃጥያትን ስቃርም
በጠላት ድለላ በእርሱ ጦር ታጅቤ
ከፍቅር አባቴ ካንተ ሲሸሽ ልቤ
እንደ ህጻን አርገህ በእርጋታ መከርከኝ
ሳላውቅ እንዳልጠፋ ፍቅርህ ሰበሰበኝ
አንተ ካስጠጋኸኝ የሚከሰኝ ማነው
ነፃ ያወጠኸኝ ከልብህ ወደህ ነው

አንተን ያገኘሁ ለት (አዝ)