ለክብር የሚሆን እቃ (Lekber Yemihon Eqa) - ዮሐንስ ፡ ግርማ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዮሐንስ ፡ ግርማ
(Yohannes Girma)

Yohannes Girma 3.jpg


(3)

አምላኬ ፡ ደስታዬ
(Amlakie Destayie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 6:11
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሐንስ ፡ ግርማ ፡ አልበሞች
(Albums by Yohannes Girma)

ጨለማ በሆነበት ብርሃንን የሚያበራ
ስለ ከበረው ፀዳልህ ሚያወራ
ሙት በገዛው ሸለቆ ሕይወትን የሚናገር
ወደ ሞት ለሚነዱት ብርሃን የሚሆን የምሥራችን የሚያበስር

  ለክብርህ የሚሆን እቃ (3 ጊዜ)
  አርገኝ ጌታ
  ለክብርህ የማያሳፍር
  ክቡር ስምህን የሚሸከም
  
  ሙሉ ማንነቱን ላንተ የሚሰጥ
  ታማኝ ባርያ የማያሳፈር (2 ጊዜ)

የወርቅ እቃ የምትለው በእሳትህ የነጠረ
የምትሻውን ልታደርግበት ያማረ
ሕያው ቅዱስ መስዋዕት አርጎ ራሱን የሰጠ
ባለህበት አብሮ የሚኖር የማይርቅ እንዳስቀመጥከው የሚቀመጥ

  ለክብርህ የሚሆን እቃ . . .

በዓለም ከሚታደለው ከጊዜያዊ ደስታ
ሰማያዊውን ለመያዝ ልዘርጋ
ዓለምን ነፍሴ ትጥላ በአይኖቼ ክብርን ትጣ
በንቀት እያየኋት ላንት ልሩጥ ፍሬን ላፍራ አንትን ላኩራ

  ለክብርህ የሚሆን እቃ . . .