ከጥዋት ፡ አንስቶ (Ketwat Ansto) - ዮሐንስ ፡ ግርማ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
Broom.png ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት
ዮሐንስ ፡ ግርማ
(Yohannes Girma)

Yohannes Girma 3.jpg


(3)

አልበም
(Amlakie Destayie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 7:08
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሐንስ ፡ ግርማ ፡ አልበሞች
(Albums by Yohannes Girma)

አቅም ፡ ስጠኝና ፡ አብዝቼ ፡ ልውደድህ
መቼም ፡ ልጥግብህ ፡ አልል ፡ አንተ ፡ አትጠገብም
ሰው ፡ ቢያንገራግር ፡ እስከሚገባው ፡ ነው
የበራለት ፡ ለታ ፡ ለመወጣት ፡ የሚያስቸግር ፡
ፍቅርህ ፡ እጂግ ፡ ብርቱ ፡ ነው

ከጥዋት ፡ አንስቶ ፡ እስከሚመሽ ፡ ድረስ
ከምሽት ፡ አንስቶ ፡ እስከንጋት ፡ ድረስ
ብትወደር ፡ አትጠገብም (፫x)
የእኔ ፡ ጌታ

እወድሃለሁ(፫x) ፡ ጌታ
እወድሃለሁ(፫x) ፡ ኢየሱስ

ላልወድህ ፡ አልችልም ፡ ላልቀርብህ ፡ አብዝቼ
የተገኘሁብህ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ምንጬ
እጅግ ፡ ጥልቅ ፡ ነው ፡ ያለን ፡ ትስስር
ከጥንት ፡ የነበረ ፡ ዛሬም ፡ ያለ
ለዘላለም ፡ የሚቀጥል ፡ ነገር

ከጥዋት ፡ አንስቶ ፡ እስከሚመሽ ፡ ድረስ
ከምሽት ፡ አንስቶ ፡ እስከንጋት ፡ ድረስ
ብትወደር ፡ አትጠገብም(፫x)
ኢየሱሴ

እወድሃለሁ(፫x) ፡ ጌታ
እወድሃለሁ(፫x) ፡ ኢየሱስ

ከጥንት ፡ ከማለዳ ፡ የእኔ ፡ የአንተ ፡ ነገር
ማቆሚያ ፡ የለውም ፡ ጊዜአቱን ፡ ሲሻገር
ሁሉ ፡ ነገር ፡ ያልፋል ፡ አንድ ፡ ሳይቀር ፡ ጠፊ ፡ ነው
ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ነገር ፡ እኔም ፡ ለአንተ ፡ ያለኝ ፡ ነገር ፡ ዘላለም ፡ ኗሪ ፡ ነው
የእኔ ፡ ጌታ

ከጥዋት ፡ አንስቶ ፡ እስከሚመሽ ፡ ድረስ
ከምሽት ፡ አንስቶ ፡ እስከንጋት ፡ ድረስ
ብትወደር ፡ አትጠገብም(፫x)
ኢየሱሴ

እወድሃለሁ(፫x) ጌታ
እወድሃለሁ(፫x) ጌታ
ኢየሱስ