Mesfin Mamo/Shilimateh Neh

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

'አንተ ግን' ሁኔታውን ስናይ እየሆነ ያለውን ከቁጥጥር ውጪየሆነ የሚመስለውን ለምን ይኼ ሁሉ እግዚአብሔር ካለ ስትል ነፍስ ስትቃትት አረ ያምላክ ያለህ አንተ ግን በዙፋንህ ተረጋግተህ ተቀምጠሃል ሁሉንም አውቀህ እግዚአብሔር ከጅማሬ እስከ ፍፃሜው ባለቤት ነህ የታሪክ ፀሐፊው ባንተ ማረፍ ነው መልካሙ ምርጫ ሌላ እኮ የለም ከተ ያለው ብልጫ ኑሮ ሲወሳሰብ ሰው ግራ ገብቶት ነገ አልታይ ብሎት ውሉ ሲጠፋበት እግዚአብሔር እያለ ለምን ይኼ ሆነ እያለ የሰው ልጅ እንቅልፍ ከዓይኑ ሸሸ አንተ ግን በዙፋንህ ተረጋግተህ ተቀምጠሃል ሁሉንም አውቀህ እግዚአብሔር ከጅማሬ እስከ ፍፃሜው ባለቤት ነህ የታሪክ ፀሐፊው ባንተ ማረፍ ነው መልካሙ ምርጫ ሌላ እኮ የለም ከቶ ያለው ብልጫ ሁሉ እኮ በእጅህ ነው ሃሳብህ ጥልቅ ነው ላመኑብህ መታመኛ እግዚአብሔር ነህ መዳኛ