Kalkidan Tilahun/Eyulign/Eyulign

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ


እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ

ግን ሰው ሳያይህ እንዴት ያደንቅሃል ሰው ሳያይህ እንዴት ያመልክሃል ያወቅንህ ግን ማቆም አቅቶናል (፪x)

እስቲ የኔን አምላክ እዩልኝ (፪x) እስቲ ኢሄንን ውብ እዩልኝ (፪x) እስቲ ኢሄንን ቆንጆ እዩልኝ (፪x) እስቲ አለባበሱን እዩልኝ (፪x)

እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ

ውበት ያለው ክብር ለው ሞገስ ያለው ውበት ያለው በሰው ብልሃት ያልተሰራ አምላክ አለ ከእኔ ጋራ (፪x)

እስቲ እግዚአብሔርን እዩልኝ (፪x) እስቲ ኢህን መልካም እዩልኝ (፪x) እስቲ ኢህንን ቸር እዩልኝ (፪x) እስቲ የእኔን አምላክ እዩልኝ (፪x)

እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ

ነፍሴ ኮበለለች እርሱን ተከትላ ሌላ ሌላ ነገር አልፈልግም ብላ (፪x)

እኔ አልፈልግም ብላ አልፈልግም ብላ (፪x)

እስቲ የእኔን አምላክ እዩልኝ (፪x) እስቲ ኢህን ጨዋ እዩልኝ (፪x) እስቲ ኢህን ኃያል እዩልኝ (፪x) እስቲ ኢህን ብርቱ እዩልኝ (፪x)

እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ

እኔማ በለሟል የአንተ አገልጋይ በቤትህ ሰራተኛ ወዳጅ ልጅህ ነኝ ባሪያህም እሆናለው በእኔ ፍላጐት ጉልበቴን ዘመኔንም ተጠቀምበት

እኔማ እኔማ እኔማ እኔማ

እኔማ በለሟል የአንተ አገልጋይ በቤትህ ሰራተኛ ወዳጅ ልጅህ ነኝ ባሪያህም እሆናለው በእኔ ፍላጐት ጉልበቴን ዘመኔንም ተጠቀምበት

ተጠቀምበት ተጠቀምበት ተጠቀምበት ተጠቀምበት

አቤቱ ውበትህ እጅግ ያስደንቃል የፊትህን ብርሃን ማን አይቶ ይቆማል (፪x)

አምልኮና ስግደት ክብር ይገባሃል

እንዳንተ ያለ ስላልተገኘ (፪x) ፍጥረት ሊያደንቅህ ሊያይህ ተመኘ (፪x) እንዳንተ ያለ ውብ ስላልተገኘ (፪x) ፍጥረት ሊያደንቅህ ሊያይህ ተመኘ (፪x)

ነበልባል ዓይኖችህን ያመረውን ፊትህን የነጠረው እግርህን እናውራው ውበትህን (፪x)

እንዳንተ ያለ ስላልተገኘ (፪x) ፍጥረት ሊያደንቅህ ሊያይህ ተመኘ (፪x)