Daniel Amdemichael/Yesew Ej Yelielebet/Yesew Ej Yelielebet
ርዕስ የሰው እጅ የሌለበት ዳንኤል አምደሚካኤል አልበምየሰው እጅ የሌለበት
አዝ አዳነኝ በፀጋው አመሰግናለሁ ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወቴ ጌታ ነው አምላክ በምህረቱ ባዘጋጀው መንገድ በወንጌሉ እምነት ሰጠኝ ዳግም ልደት
በደስታ ከመዘመር ከማመስገን በቀር እኔማ ምን ልከፍል ከቶ ምን ልናገር የሰው እጅ የሌለበት የእኔ ብሎ የሚያኮራ በማመን የሚገኝ ጽድቅ የመስቀሉን ስራ
ፀጋው በእምነት ሆኖ አድኖኛል እግዚአብሔር በልጁ ሕይወትን ሰጥቶኛል ሁሉ ተፈጸመ በመስቀሉ በሰላም እንድኖር በዘለዓለም ፍቅሩ
ላመስግነው በዝማሬ ይኼን ታላቅ ጌታ ከጨለማ ለነጠቀኝ ከዚያ ክፉ ቦታ ለወደደኝ ብርሃኑን ላበራ በሕይወቴ መልካም ዜማ ለእርሱ ይሁን ይክበር መድሃኒቴ
አምላክ አበጃጀው ዘለዓለሜን አንድ ልጁን ሰጥቶ ክርስቶስ ብቃቴን የዘለላእም ህብረት ከአብ ጋራ አገኘሁ ልጅነት በክርስቶስ ስራ
ምሥጋናውን ልዘምረው ልናገር ወንጌሉን ጌታ ኢየሱስ እንደሚያድን ላብስር ምስራቹን የአምላክ ፍቃድ ኢኼ ሆኗል ሰዎን የሚያመልጡበት በልጁ ደም በእግዚአብሔር ጽድቅ አምነው ሚድኑበት
አዝ አዳነኝ በፀጋው አመሰግናለሁ ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወቴ ጌታ ነው አምላክ በምህረቱ ባዘጋጀው መንገድ በወንጌሉ እምነት ሰጠኝ ዳግም ልደት
በደስታ ከመዘመር ከማመስገን በቀር እኔማ ምን ልከፍል ከቶ ምን ልናገር የሰው እጅ የሌለበት የእኔ ብሎ የሚያኮራ በማመን የሚገኝ ጽድቅ የመስቀሉን ስራ
ምሥጋና ለአምላክ ፍቅር ለታደገኝ እግሬን ከጨለማ መንገድ መለሰልኝ ብርሃንን አሳየኝ ቅዱስ ቃሉ ተፈጸመ እንዳለ ጌታ በመስቀሉ
ባመሰግን ይበዛል ወይ እኔስ በየእለቱ
ቅኔ ብቀኝ ባሸበሸብ ብዘምር በቤቱ
እልልስ ብል በታላቅ ድምጽ ብጮህ እስከደስታ
ባጨበጭብ በመቅደሱ ለዚህ ክቡር ጌታ
አዝ አዳነኝ በፀጋው አመሰግናለሁ ኢየሱስ ክስቶስ የሕይወቴ ጌታ ነው አምላክ በምህረቱ ባዘጋጀው መንገድ በወንጌሉ እምነት ሰጠኝ ዳግም ልደት
በደስታ ከመዘመር ከማመስገን በቀር እኔማ ምን ልከፍል ከቶ ምን ልናገር የሰው እጅ የሌለበት የእኔ ብሎ የሚያኮራ በማመን የሚገኝ ጽድቅ የመስቀሉን ስራ አሃ (፬x)