Daniel Amdemichael/Yesew Ej Yelielebet/Yemayelewawet
ዘማሪ ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል እግዚአብሔር ብቻ ነው እግዚአብሔር ብቻ አዝ ነገር እንደነበረ እንዳለ አይቀርም (፪x) የማይለዋወጥ የማይቀያየር ጸንቶ የሚኖረው እግዚአብሔር ብቻ ነው (፪x)
ዝና ክብር ቋሚ አይደለም ሃብት አያኖር ለዘለዓለም ዓለም መልኳ ተለዋጭ ነው ያው የሆነው ክርስቶስ ነው ሕይወት ኢየሱስ ነው አዝ ነገር እንደነበረ እንዳለ አይቀርም (፪x) የማይለዋወጥ የማይቀያየር ጸንቶ የሚኖረው እግዚአብሔር ብቻ ነው (፪x)
ትላንት ዛሬም ለዘለዓለም ያው የሆነው ቤዛ ለዓለም ማይለወጥ ማያረጀው ጌታ ብቻ የማይሞተው ትንሳኤ ሕይወት ነው አዝ ነገር እንደነበረ እንዳለ አይቀርም (፪x) የማይለዋወጥ የማይቀያየር ጸንቶ የሚኖረው እግዚአብሔር ብቻ ነው (፪x)
ፀሐይ ብርሃን ስትከለክል ጨረቃዋም ደም ስትመስል ዓለም አላት መጨረሻ ያለ ሚኖር ጌታ ብቻ የዘለዓለም አምባ አዝ ነገር እንደነበረ እንዳለ አይቀርም (፪x) የማይለዋወጥ የማይቀያየር ጸንቶ የሚኖረው እግዚአብሔር ብቻ ነው (፪x)
"እግዚአብሔር ብቻ ነው እግዚአብሔር ብቻ (፬x)"
የሚመጣ አሀአሀ የሚከበር አሀአሀ የሚነግስ ኢየሱስ። አዝ ተቀናቃኝ የለው ወይንም ባላጋራ ፊት ለፊት የሚቆም ግጥሚያ ከእሱ ጋራ /2/ በአህዛብም ፊት በክብር ይገለጣል ብንወድም ባንወድም ኢየሱስ ይነግሳል /2/ አዝ ከእንግዲህ ለውርደት ለሞት አይሰጥም አንድ ጊዜ በመስቀል ፈጽሟል ሁሉንም /2/ ያኔ ዕዳ ሊከፍል ዛሬ ዳኛ ሆኖ ይመጣል ጌታችን በክብር ተክኖ። /2/ አዝ ከዘመናት በፊት ሁሉን ጥለው ያሉ ለእሱ የተገዙ ሞፈር ቀንበር ሳይሉ /2/ በታላቅ ዕልልታ በሆታ በደስታ በአይናቸው ያዩታል ዘለዓለም ጌታ /2/