From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዬ
ደረሰልኝ ፡ ተራዬ
ደረሰልኝ ፡ ተራዬ
ላንሳ ፡ በገናዬን (፪x)
ደረሰልኝ ፡ ተራዬ
ደረሰልኝ ፡ ተራዬ
ላንሳ ፡ በገናዬን (፪x)
እባቡን ፡ ጊንጡንም ፡ አየረጋገጠ
አስማቱን ፡ መተቱን ፡ ድግምቱን ፡ ሟርቱን ፡ እየገለበጠ (አሄ)
እለፍ ፡ አለኝ ፡ ጌታ ፡ መንገዴን ፡ ከፋፍቶ
የሚያስፈራራውን ፡ ጠላቴንም ፡ መቶ
እለፍ ፡ አለኝ ፡ ጌታ ፡ መንገዴን ፡ ከፋፍቶ
የሚያስፈራራውን ፡ ጠላቴንም ፡ መቶ
በሞትና ፡ በእኔ ፡ አንድ ፡ እርምጃ ፡ ቀርቶ
ጌታም ፡ ከመሻሸ ፡ መጥቶ
የቀደመኝ ፡ መስሎት ፡ ከፊት ፡ ፊት ፡ የሮጠው
ዘግይቶ ፡ የመጣ ፡ አምላኬ ፡ ቀደመው (፪x)
ቀደመው ፡ አሆ (፬x)
ቀደመው ፡ አሆ (፬x)
ደረሰልኝ ፡ ተራዬ
ደረሰልኝ ፡ ተራዬ
ላንሳ ፡ በገናዬን (፪x)
ደረሰልኝ ፡ ተራዬ
ደረሰልኝ ፡ ተራዬ
ላንሳ ፡ በገናዬን (፪x)
እባቡን ፡ ጊንጡንም ፡ አየረጋገጠ
አስማቱን ፡ መተቱን ፡ ድግምቱን ፡ ሟርቱን ፡ እየገለበጠ (አሄ)
እለፍ ፡ አለኝ ፡ ጌታ ፡ መንገዴን ፡ ከፋፍቶ
የሚያስፈራራውን ፡ ጠላቴንም ፡ መቶ
እለፍ ፡ አለኝ ፡ ጌታ ፡ መንገዴን ፡ ከፋፍቶ
የሚያስፈራራውን ፡ ጠላቴንም ፡ መቶ
አልተኛም ፡ ለሰይጣን ፡ እንቅልፍ ፡ አይወስደኝ
መንገድ ፡ ላይ ፡ ሊያስቀረኝ ፡ ለሚተጋብኝ (፪x)
ይፈልጋል ፡ እንጂ ፡ ከመንገድ ፡ ሊያስቀረኝ
ጠላቴ ፡ የማይደፍረው ፡ ብርቱ ፡ ቅጥር ፡ አለኝ
ይፈልጋል ፡ እንጂ ፡ ከመንገድ ፡ ሊያስቀረኝ
ጠላቴ ፡ የማይደፍረው ፡ ብርቱ ፡ ቅጥር ፡ አለኝ
ብርቱ ፡ ነህ ፡ አሆ (፫x)
ብርቱ ፡ ቅጥር ፡ አለኝ
ብርቱ ፡ ነህ ፡ አሆ (፫x)
ብርቱ ፡ ቅጥር ፡ አለኝ
|