Yosef Kassa/Nuroyie Bekidan New/Kengedihema

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ ዮሴፍ ካሳ ርዕስ ከእንግዲህማ አልበም ኑሮዬ በኪዳን ነው

ፊቴ የቆመውን ባሕር ያኔ አሳልፎኝ ነበር ዛሬስ ደግሞ ሌላው ቢገጥመኝ በየተራ ቢሰለፍብኝ ዓይኔን ማንከራተቱን ትቼ ልምታ ከበሮዬን አንስቼ የሰልፉ ጌታ ከእኔ ጋር ነው ዛሬም ጠላቴን ሊያዋርደው (፪x)

ያሻገረኝ ጌታ ያን የትላንቱን (፫x) አሁንም ይሰራል ያን ሃይሉን ሳምን (፫x) በእውነት ላመልከው ከልቤ ስነሳ (፫x) ሁሉን አሳመረው የይሁዳ አንበሳ (፫x)

አዝ ከእንግዲህማ ወስኗል ልቤ ከእንግዲህማ ምንም ላይፈራ ከእንግዲህማ ጌታ ኢየሱስ እያለ ከእኔ ጋራ ከእንግዲህማ ሌላውን አልሰማም ከእንግዲህማ ከንቱ ነውና ከእንግዲህማ እዘምራለው ከልቤ ለእርሱ ምሥጋና ከልቤ ለእርሱ ምሥጋና ከልቤ ለእርሱ ምሥጋና ኢየሱስ ጌታ ነውና ኢየሱስ ጌታ ነውና (፪x)

ፊቴ የቆመውን ባሕር ያኔ አሳልፎኝ ነበር ዛሬስ ደግሞ ሌላው ቢገጥመኝ በየተራ ቢሰለፍብኝ ዓይኔን ማንከራተቱን ትቼ ልምታ ከበሮዬን አንስቼ የሰልፉ ጌታ ከእኔ ጋር ነው ዛሬም ጠላቴን ሊያዋርደው

የቆመው ተራራ ፊቴ ተከምሮ (፪x) አይመስልም ሚታለፍ እንደሚከብድ ሆኖ (፪x) ለእኔ እንጂ ለአምላኬ መቼ አስቸገረው (፪x) በተአምራቱ ሁሉን ሜዳ አደረገው (፪x) አዝ ከእንግዲህማ ወስኗል ልቤ ከእንግዲህማ ምንም ላይፈራ ከእንግዲህማ ጌታ ኢየሱስ እያለ ከእኔ ጋራ ከእንግዲህማ ሌላውን አልሰማም ከእንግዲህማ ከንቱ ነውና ከእንግዲህማ እዘምራለው ከልቤ ለእርሱ ምሥጋና ከልቤ ለእርሱ ምሥጋና ከልቤ ለእርሱ ምሥጋና ኢየሱስ ጌታ ነውና ኢየሱስ ጌታ ነውና (፬x)