ስንቱን ፡ ላውራ (Sentun Lawra) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yoseph Bekele)

Lyrics.jpg


(3)

ስንቱን ፡ ላውራ
(Sentun Lawra)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yoseph Bekele)

 
በመከራዬ ፡ ቀን ፡ ላልተለየኝ
አበሳዬን ፡ ከኔ ፡ ላራቀልኝ
ለዚህ ፡ ለጌታዬ ፡ እሰግዳለሁ
ሁልጊዜ ፡ ምሥጋናን ፡ አበዛለሁ
ዘምርለታለሁ (፭x) ፡ ለአባቴ ፡ ዘምርለታለሁ

አዝ፦ ስንቱን ፡ ላውራው ፡ ልተርከው
አንተ ፡ ያደረከው ፡ ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ጌታ
ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው (፬x)

ፊትለፊት ፡ ቆሞ ፡ ከፍ ፡ ያለ ፡ ተራራ
የመድሃኒቴ ፡ አምላክ ፡ ስልህ ፡ ሰማኸኝ ፡ ስጣራ
በተራራዬ ፡ ላይ ፡ በድል ፡ አራመድከኝ
ከሳሶቼ ፡ እያዩ ፡ አሜን ፡ ተስፋዬን ፡ ወረስኩኝ
ተስፋዬን ፡ ሰበርኩት

አዝ፦ ስንቱን ፡ ላውራው ፡ ልተርከው
አንተ ፡ ያደረከው ፡ ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ጌታ
ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው (፬x)

ተስፋዬን ፡ ቆርጬ ፡ ለሰው ፡ ያልነገርኩት
አበቃለት ፡ ብዬ ፡ ሞቶ ፡ የቀበርኩት
ምንተስኖህ ፡ ጌታ ፡ ሁሉ ፡ ተችሎሃል
አንገት ፡ ያስደፋኝን ፡ ቀንበሬን ፡ ሰብረሃል ፡ ጌታ
ቀንበሬን ፡ ሰብረሃል

አዝ፦ ስንቱን ፡ ላውራው ፡ ልተርከው
አንተ ፡ ያደረከው ፡ ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ጌታ
ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው (፬x)

አዋጅ ፡ ሲል ፡ ጠላቴ ፡ እኔን ፡ ሊያጠፋ
ከበሮ ፡ ሲያስደልቅ ፡ ነጋሪት ፡ ሲያስመታ
በአንድ ፡ ሌሊት ፡ ጀምበር ፡ ታሪክ ፡ ተቀየረ
ጠላት ፡ በቆፈረው ፡ አሜን ፡ ጉድጓድ ፡ ተቀበረ ፡ እሰይ
ጉድጓድ ፡ ተቀበረ

በመከራዬ ፡ ቀን ፡ ላልተለየኝ (ላልተለየኝ)
አበሳዬን ፡ ከኔ ፡ ላራቀልኝ (ላራቀልኝ)
ለዚህ ፡ ለጌታዬ ፡ እሰግዳለሁ
ሁልጊዜ ፡ ምሥጋናን ፡ አበዛለሁ ፡ ዘምርለታለሁ አዎ
ዘምርለታለሁ ፡ (ዘምርለታለሁ) (፪x)
ዘምርለታለሁ ፡ ለአባቴ ፡ ዘምርለታለሁ (አቤት ፡ አቤት)

አዝ፦ ስንቱን ፡ ላውራ (ላውራ) ፡ ልተርከው (ልተርከው)
አንተ ፡ ያደረከው (ያደረከው)
ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ጌታ (በላይ ፡ በላይ ፡ ነው)
ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው (፬x) (በላይ ፡ በላይ)