ያህዌ ፡ ንሴ (Yahwe Nsie) - ዮሐንስ ፡ ግርማ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሐንስ ፡ ግርማ
(Yohannes Girma)

Yohannes Girma 3.jpg


(3)


(4)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 6፡25
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሐንስ ፡ ግርማ ፡ አልበሞች
(Albums by Yohannes Girma)

ሰንደቅ አላማዬን እግዚአብሔርን ይዤ
በቀንም በለሊት ክንዱን ተንተርሼ
በሚሆነው ሁሉ ልቤ አይናወጥ
በመዓበሉም መሀል ታምኜ ብቀመጥ
በድል እንድራመድ እግዚአብሔር ሃይሌ ነው
ሽለቆን ተራራን አብሮኝ ሚሻገረው
በደስታም በኀዘን እርሱ አብሮኝ አለ
ከአባቴ ጋር ነኝ የሚያስፈራኝ የለም

ያህዌ ንሲ(፫) X5

ለተቀደሰ አላማ የጠራኝ
ከትቢያ አንስቶ በዘይቱ የቀባኝ
በህልም ቅዠቴ በእውን በ ደሜ እየሱስ አላማዬ(፪)

በርሀቡ ዘመን እየሱስ ጥጋቤ ነው
ስገፋ ስነቀፍ እርሱ ወደ እኔ ነው
ለሰዎች ችግሬ አይገባ ይሆናል
ጌታ እግዚአብሔር ግን ቋንቋዬን ይረዳል
የሰማዩ አባት የፈጠረኝ ጌታ
ሲጠብቀኝ ኖረ ሲመሽም ሲነጋ
እርሱን አላማዬ ጌታዬ ህያውነህ
ለእርሱ ሁሉን ነግሬ ታምኜ እጓዛለሁ
ያህዌ ንሲ(፫) x5

ለተቀደሰ አላማ የጠራኝ
ከትቢያ አንስቶ በዘይቱ የቀባኝ
በህልም ቅዠቴ በእውን በደሜ እየሱስ አላማዬ(፪)

የሚከተለውን አውቆ የሚጓዝ ሰዉ
ህያው እግዚአብሔርን አላማው ያረገው
ጌታው ከበፊት በእምነት እያየ
ከአለም እርኩሰት እራሱን የለየ
መታመኛው ለእርሱ እግዚአብሔር ይሆናል
በሚያስፈራም ዘመን ያለስጋት ያልፋል
ለቤት ለጎረቤት ለአለም ብርሃን ነው
አምላኩ አርፎበት እንደልቤ የሚለው

ያህዌ ንሲ(፫) x5

ለተቀደሰ አላማ የጠራኝ
ከትቢያ አንስቶ በዘይቱ የቀባኝ
በህልም ቅዠቴ በእውን በደሜ እየሱስ አላማዬ(፪)

የአለምን ፉጨት የሚሰማ ጆሮ
ብልጭልጭ ሸቀጧን የሚመኝ አዕምሮ
ከኔ ዘንድ ተነቅሎ መታሰቢያም የለው
ለክፉዎች ጩኸት እንዲሁ የቅዠት ነው
ይልቁን እየሱስ በእኔ ላይ ጌታ ነው
መንፈሴን ስጋዬን ነፍሴን የሚገዛው
የእርሱ ወታደር ነኝ ጠላትን ተዋጊ
አምላኬ እማ እያለ ክፉን አንበርካኪ

ያህዌ ንሲ(፫) x5

ለተቀደሰ አላማ የጠራኝ
ከትቢያ አንስቶ በዘይቱ የቀባኝ
በህልም ቅዠቴ በእውን በደሜ እየሱስ አላማዬ(፪)