ብዙ ፡ ምርኮ (Bizu Mirko) - ዮሐንስ ፡ በላይ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሐንስ ፡ በላይ
(Yohannes Belay)

Lyrics.jpg


(1)

ትችላለህ
(Techelaleh)

ዓ.ም. (Year): 2009
ቁጥር (Track):

(1)

ጸሐፊ (Writer): ዮሐንስ ፡ በላይ
(Yohannes Belay
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሐንስ ፡ በላይ ፡ አልበሞች
(Albums by Yohannes Belay)

ብዙ ምርኮ እንዳገኘ ሰው
በቃልህ ልቤን ደስ አለው
ብዙ ምርኮ እንዳገኘ ሰው
የሱስ ባንተ ልቤን ደስ አለው

አለው በጌታ ደስ አለው
ውስጤ በጌታ ደስ አለው
አለው በጌታ ደስ አለው
ልቤ በጌታ ደስ አለው

ለክብርህ ልዘምር በገና ሳነሳ
ልቤን ደስ ደስ አለው ካንተ የተነሳ
ለቃልህ ስዘምር በገና ሳነሳ
ውስጤን ደስ ደስ አለው ካንተ የተነሳ

ሌላ የለኝም በልቤ አንተ አንተ ነህ ወዳጄ
ሌላ የለኝም በውስጤ አንተ አንተ ነህ ወዳጄ

አንተው ነህ ምታመንህ አንተው ነህ ምደገፍብህ
አንተው ነህ ተወራርጄ አንተው ነህ ያላፈርኩብህ
አንተው ነህ ቤዛ የሆንከኝ አንተው ነህ መደገፊያዬ
አንተው ነህ አንተ ብቻ ነህ አንተው ነህ ለኔስ ጌታዬ

አንተው ነህ ጨለማዬን አንተው ነህ የገፈፍክልኝ
አንተው ነህ በብርሃንህ አንተው ነህ የለወጥክልኝ
አንተው ነህ መደገፊያዬ አንተው ነህ መታመኛዬ
አንተው ነህ መደገፊያዬ አንተው ነህ መታመኛ

ቃልህ ከማር ይልቅ እጅግ ይጣፍጣል
ለነፍሴ መፅናኛ ማረፊያ ሆኗታል

ሌላ የለኝም በልቤ አንተ አንተ ነህ ወዳጄ
ሌላ የለኝም በውስጤ አንተ አንተ ነህ ወዳጄ

አንተው ነህ ምታመንህ አንተው ነህ ምደገፍብህ
አንተው ነህ ተወራርጄ አንተው ነህ ያላፈርኩብህ
አንተው ነህ ቤዛ የሆንከኝ አንተው ነህ መደገፊያዬ
አንተው ነህ አንተ ብቻ ነህ አንተው ነህ ለኔስ ጌታዬ

አንተው ነህ ጨለማዬን አንተው ነህ የገፈፍክልኝ
አንተው ነህ በብርሃንህ አንተው ነህ የለወጥክልኝ
አንተው ነህ መደገፊያዬ አንተው ነህ መታመኛዬ
አንተው ነህ መደገፊያዬ አንተው ነህ መታመኛ