From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
የነፍሴ ፡ ቋንቋ ፡ ነህ ፡ (የሕይወቴ ፡ ዜና) ፪X
ማወደስ ፡ የማደንቅ ፡ (የአንተን ፡ ልእልና)፪X ፡
የእኔ ፡ ተልእኮ ፡ ነው ፡ ጥሪና ፡ ውሳኔ
እስትንፋሴ ፡ እስካለች ፡ ቀሪውን ፡ ዘመኔ
ኢየሱስ ፡ ላድንቅህ ፬X
በፏፏቴው ፡ ውበት ፡ (እጆችህ ፡ ባበጁት)፪X
በተፈጥሮ ፡ ቀለም ፡ (ሁሉን ፡ ባቆነጁት)፪X
ግርምቴም ፡ አይበቃ ፡ (ዝም ፡ አይልም ፡ አፌ)፪X
ምሥጋና ፡ ይፈልቃል ፡ (ከመስክ ፡ ከደጃፌ)፪X
የተፈጠርኩበት ፡ የምድር ፡ ላይ ፡ ኑሮ
የተፃፈልኝም ፡ ሁሉም ፡ ተቀምሮ
አንተን ፡ ማወደስ ፡ ነው ፡ ክበር ፡ ክበር ፡ ማለት
ጅማረው ፡ ፊፃሜ ፡ (የሕይወቴ ፡ መሠረት)፪X
የነፍሴ ፡ ቋንቋ ፡ ነህ ፡ (የሕይወቴ ፡ ዜና) ፪X
ማወደስ ፡ የማደንቅ ፡ (የአንተን ፡ ልእልና)፪X ፡
የእኔ ፡ ተልእኮ ፡ ነው ፡ ጥሪና ፡ ውሳኔ
እስትንፋሴ ፡ እስካለች ፡ ቀሪውን ፡ ዘመኔ
ኢየሱስ ፡ ላድንቅህ ፬X
የሰማዩ ፡ ቀለም ፡ (የአድማሳቱ ፡ ግርማ)፪X
የንፋሱ ፡ ፉጨት ፡ (የአዋፋቱ ፡ ዜማ) ፡ ፪X
ክብርህን ፡ መናገር ፡ (ውዳሴን ፡ ማሳረግ)፪X
ዝናህን ፡ መተረክ ፡(ከፍ ፡ ከፍ ፡ ማድረግ)፪X
የተፈጠርኩበት ፡ የምድር ፡ ላይ ፡ ኑሮ
የተፃፈልኝም ፡ ሁሉም ፡ ተቀምሮ
አንተን ፡ ማወደስ ፡ ነው ፡ ክበር ፡ ክበር ፡ ማለት
ጅማረው ፡ ፊፃሜ ፡ (የሕይወቴ ፡ መሠረት)፪X
|