ክብሬ (Kibre) - ዮሐንስ ፡ በላይ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሐንስ ፡ በላይ
(Yohannes Belay)

Lyrics.jpg


(4)

ላድንቅህ
(Ladenekeh)

ዓ.ም. (Year): 2018
ቁጥር (Track):

(10)

ጸሐፊ (Writer): ዮሐንስ ፡ በላይ
(Yohannes Belay
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሐንስ ፡ በላይ ፡ አልበሞች
(Albums by Yohannes Belay)

ባዶነቴ ባንተ ሲሞላ
ምን ይታሰበኛል ከማመስገን ሌላ
ካንተ እየተቀበልኩ ላንተ እሰጣለው
ደግሜ ደግሜ እባርክሃለው

ክብሬ ልዘምርልህ/2
እየሱስ ልዘምርልህ/2

ፊትህን እንድሻ ክንዴ በረታልኝ
ማለዳ ማለዳ እየፈሰስክልኝ
የህይወት ትርጉሙ ባንተ ተፈታልኝ
ከእግርህ ስር ቅጭ ብዬ አባት ሆነህልኝ

ክንዴም አይታጠፍ ጉልበቴም አይዝል
ክፍታን ትቼ አላይም ቁልቁል
መላው እኔነቴ የተወረሰበት
መንፈስ ቅዱስ አለኝ የምበረታበት

ክብሬ ልዘምርልህ/2
እየሱስ ልዘምርልህ/2

ባዶነቴ ባንተ ሲሞላ
ምን ይታሰበኛል ከማመስገን ሌላ
ካንተ እየተቀበልኩ ላንተ እሰጣለው
ደግሜ ደግሜ እባርክሃለው

ክብሬ ልዘምርልህ/2
እየሱስ ልዘምርልህ/2

የህይወት ወጣ ገባ ዳገት ቁልቁለቱ
ግራ እንዳይገባኝ ግለት ትኩሳቱ
አላይ ወደግራ አላይ የቀኜን
አንተኑ ሰማለው ውስጤ ያለውን

ክንዴም አይታጠፍ ጉልበቴም አይዝል
ክፍታን ትቼ አላይም ቁልቁል
መላው እኔነቴ የተወረሰበት
መንፈስ ቅዱስ አለኝ የምበረታበት

ክብሬ ልዘምርልህ/2
እየሱስ ልዘምርልህ/2

ክብሬ/3
ክብሬ ነህ ሞገሴ