ሃሳቤን ፡ ፈውሰው (Hasaben Fewesew) - ዮሐንስ ፡ በላይ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሐንስ ፡ በላይ
(Yohannes Belay)

Yohannes Belay 2.jpg


(2)

ሃሳቤን ፡ ፈውሰው
(Hasaben Fewesew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሐንስ ፡ በላይ ፡ አልበሞች
(Albums by Yohannes Belay)

ጌታ ፡ ለስሜቴ ፡ ለሥጋዬ
ለራሴ ፡ ለፍላጐቴ
አትስጠኝ(፫) ፡ ቸሩ ፡ አባቴ

ሃሳቤን ፡ ፈውሰው(፪)

ክፋትን ፡ ለማድረግ ፡ ቁጭ ፡ ብዬ ፡ ባስበው
በመኝታዬ ፡ ሆኜ ፡ ባሰላስለው
ነግቶ ፡ ላላደርገው ፡ ዋስትና ፡ የለኝም
ኃይልም ፡ በእጄ ፡ ነው ፡ ከቶ ፡ አያቅተኝም

ሃሳቤን ፡ ፈውሰው (፪)

ክፉ ፡ አድራጊዎችን ፡ አንተ ፡ ትጠላለህ
የጠማማውን ፡ መንገድ ፡ ትቃወመዋለህ
አልሁንብህ ፡ ጌታ ፡ እንደምትጠላቸው
የድርጊቴ ፡ ምንጩን ፡ ሃሳቤን ፡ ፈውሰው

ሃሳቤን ፡ ፈውሰው (፪)