ክብር ፡ ይሁን ፡ ለስሙ (Keber Yehun Lesemu) - ይድነቃቸው ፡ ተካ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ይድነቃቸው ፡ ተካ
(Yidnekachew Teka)

Yidnekachew Teka 1.jpeg


(1)

ቸኮለብኝ ፡ ልቤ ፡ ሊያገኝህ
(Chekolebegn Lebie Liyagegnh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የይድነቃቸው ፡ ተካ ፡ አልበሞች
(Albums by Yidnekachew Teka)

 
ክብር ይሁን ለስሙ

1/ በፈረስ፡ ውድድር፡ ወደ፡ ትግሉ፡ ሜዳ
ሁሉም፡ ተሰማርቶ፡ ድንገት፡ ድል፡ ቢሰማ
ተብሎ፡ ቢጠየቅ፡ "ማነው ያሸነፈው?"
ፈረስና፡ ጌታው፡ አንድ፡ ላይ፡ ተቀምጠው

"እኔ፡ ነኝ!" 'ሚለውን፡ እስኪ፡ ይጠየቅ፡ ማነው?
ጌታው፡ አይደለም፡ ወይ፡ ፈረሱን፡ እያየው?
እንዲህ፡ ሲል፡ ሰማሁት፣ እንዲህ፡ ሲል፡ አምላኬ
"ድል፡ አድርጌያለሁኝ፤ እኔማ፡ በራሴ"
ስለዚህ፡ ስንኖር፡ በዚህች፡ ምድር፡ ላይ
አምላክ፡ እንዳለው፡ ሰው፡ እንደ፡ ተወካይ
ስለእኛ፡ ለሞተው፡ ደግሞ፡ ለተነሳው
የእርሱን፡ ክብር፡ እንጂ፡ የእኛን፡ ስም፡ እንርሳው!

ክብር፡ ይሁን፤ ለዝናው!
ክብር፡ ይሁን፤ ለስሙ!
ክብር፡ ይሁን፤ ዘለዓለም!
ክብር፡ ለተገባው!

ክብር፡ ይሁን፤ ለዝናው!
ክብር፡ ይሁን፤ ለስሙ!
ክብር፡ ይሁን፤ ዘለዓለም!
ክብር፡ ለተገባው!

2/ በሩጫ፡ ውድድር፡ ወደ፡ ሩጫው፡ ሜዳ
ሁሉም፡ ተሰማርቶ፡ ድንገት፡ ድል፡ ቢሰማ
ቶሎ፡ የሚይዙት፡ ሮጠው፡ ይሄዱና
ባንዲራውን፡ አይደል፡ ሊለብሱት፡ በተርታ?

የወከላቸውን፡ አገር፡ መቼ፡ ረሱ
ለስማቸው፡ ብቻ፡ አይሮጡም፡ እነርሱ 
እንዲህ፡ ሲል፡ ሰማሁት፣ እንዲህ፡ ሲል፡ አምላኬ
"ድል፡ አድርጌያለሁኝ፤ እኔማ፡ በራሴ"
ስለዚህ፡ ስንኖር፡ በዚህች፡ ምድር፡ ላይ
አምላክ፡ እንዳለው፡ ሰው፡ እንደ፡ ተወካይ
ስለእኛ፡ ለሞተው፡ ደግሞ፡ ለተነሳው
የእርሱን፡ ክብር፡ እንጂ፡ የእኛን፡ ስም፡ እንርሳው!

ክብር፡ ይሁን፤ ለዝናው!
ክብር፡ ይሁን፤ ለስሙ!
ክብር፡ ይሁን፤ ዘለዓለም!
ክብር፡ ለተገባው!

ክብር፡ ይሁን፤ ለዝናው!
ክብር፡ ይሁን፤ ለስሙ!
ክብር፡ ይሁን፤ ዘለዓለም!
ክብር፡ ለተገባው!

(የኔ፡ ጌታ) መሆን፡ ያማረህን
(የኔ፡ ኢየሱስ) እኔ፡ ስኖር፡ በምድር
(የኔ፡ ጌታ) በእኔ፡ አልፈህ፡ ሁንብኝ
(የኔ፡ ኢየሱስ) ኢየሱስ፡ ይኸውነኝ

(የኔ፡ ጌታ) መሆን፡ ያማረህን
(የኔ፡ ኢየሱስ) እኔ፡ ስኖር፡ በምድር
(የኔ፡ ጌታ) በእኔ፡ አልፈህ፡ ሁንብኝ
(የኔ፡ ኢየሱስ) ኢየሱስ፡ ይኸውነኝ

3/ ኢየሱስ፡ ተቀምጦባት፡ በዚያች፡ ውርንጭላ
ወደ፡ ኢየሩሳሌም፡ በክብር፡ ሲገባ
"ሆሣዕና!" ሲባል፡ ሲዘመር፡ ለክብሩ
ዘንባባው፡ ሲነጠፍ፡ ሁሉም፡ "ኦሆ!" እያሉ

ብትረግጠውም፡ እንኳን፡ ውርንጭላዪቱ
ያነጠፉለትን፡ ሲገባ፡ ንጉሡ
ለእርሷ፡ አይደለም፡ ከቶ፡ ይኼ፡ ሁሉ፡ ሙገሳ
በፊት፡ ማን፡ አይቷታል፡ ባለችበት፡ ታስራ?
እኛንም፡ ኢየሱስ፡ ከፈታን፡ ለክብሩ
ልቡ፡ ከወደደ፡ ሊሠራብን፡ እርሱ
ጌታ፡ መርጦን፡ እንጂ፡ ምን፡ ተገኝቶ፡ በእኛ?
የማንጠቅም፡ ባሮች፡ አይደለን፡ ወይ፡ እኛ?

ክብር፡ ይሁን፤ ለዝናው!
ክብር፡ ይሁን፤ ለስሙ!
ክብር፡ ይሁን፤ ዘለዓለም!
ክብር፡ ለተገባው!

ክብር፡ ይሁን፤ ለዝናው!
ክብር፡ ይሁን፤ ለስሙ!
ክብር፡ ይሁን፤ ዘለዓለም!
ክብር፡ ለተገባው!

4/ ሁለት፡ ባሮች፡ ታግለው፡ በጥንቱ፡ ጨዋታ
አንደኛው፡ ሲሸነፍ፡ አንዱ፡ ድል፡ ሲነሳ
ሕዝቡ፡ ይነሳና፡ ለአሸናፊው፡ ጌታ
ይጨፍርለታል፡ ባሪያው፡ እየሰማ

ምንም፡ ቢያሸንፍ፡ ባሪያው፡ በጉልበቱ
ጌታው፡ ዋጋ፡ ከፍሎ፡ አድርጐታል፡ የራሱ
እንዲህ፡ ሲል፡ ሰማሁት፣ እንዲህ፡ ሲል፡ አምላኬ
"ድል፡ አድርጌያለሁኝ፤ እኔማ፡ በራሴ"
ስለዚህ፡ ስንኖር፡ በዚህች፡ ምድር፡ ላይ
አምላክ፡ እንዳለው፡ ሰው፡ እንደ፡ ተወካይ
ስለእኛ፡ ለሞተው፡ ደግሞ፡ ለተነሳው
የእርሱን፡ ክብር፡ እንጂ፡ የእኛን፡ ስም፡ እንርሳው!

ክብር፡ ይሁን...