ከእሳት ፡ ውስጥ ፡ የነጠቀኝ (Kesat West Yeneteqegn) - ወርቅነህ ፡ አላሮ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ወርቅነህ ፡ አላሮ
(Workneh Alaro)

Workneh Alaro 1.jpg


(1)

ከእሳት ፡ ውስጥ ፡ የነጠቀኝ
(Kesat West Yeneteqegn)

ዓ.ም. (Year): ዓ.ም. (Year)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የወርቅነህ ፡ አላሮ ፡ አልበሞች
(Albums by Workneh Alaro)

አዝ፦ ከእሳት ፡ ውስጥ ፡ የነጠቀኝ
በሕይወት ፡ ኑር ፡ ያለኝ
ያዳነኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x)
የራራልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው

አበሳዬን ፡ ሁሉ ፡ አራቀ
እድፋሙን ፡ ልብሴን ፡ ቀየረው (፪x)
ሰይጣንን ፡ ገሰጸው
እርሱ ፡ እኮ ፡ ልጄ ፡ ነው ፡ አለው
የእኔ ፡ ነው ፡ ብሎ ፡ አባረረው

አዝ፦ ከእሳት ፡ ውስጥ ፡ የነጠቀኝ
በሕይወት ፡ ኑር ፡ ያለኝ
ያዳነኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x)
የራራልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው

ጠላት ፡ ዘባበተብኝ
አምላክህ ፡ እስቲ ፡ ያድንህ ፡ አለኝ
መጨረሻህ ፡ ዛሬ ፡ ነው ፡ አለኝ
የተዋረዱትን ፡ የሚያይ ፡ ከተፍ ፡ አለልኝ ፡ ከሰማይ
እንደእርሱ ፡ ማነው ፡ ኤልሻዳይ

አዝ፦ ከእሳት ፡ ውስጥ ፡ የነጠቀኝ
በሕይወት ፡ ኑር ፡ ያለኝ
ያዳነኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x)
የራራልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው

እግዚአብሔር ፡ ለካ ፡ መልስ ፡ አለው
ዙሪያዬን ፡ ለከበበኝ
ሊወግረኝ ፡ ድንጋይ ፡ ላነሳን
አቤት ፡ የማዳን ፡ ጥበቡ
የማይመረመር ፡ ነው ፡ ፍርዱ
በዕልልታ ፡ ለእርሱ ፡ ስገዱ

አዝ፦ ከእሳት ፡ ውስጥ ፡ የነጠቀኝ
በሕይወት ፡ ኑር ፡ ያለኝ
ያዳነኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x)
የራራልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው

ሰይጣን ፡ በብርቱ ፡ ከሰሰኝ
በኀጢአቴ ፡ እንዲፈረድብኝ
____ ፡ እንዲ ፡ ____ ፡ ከበበ
ጠበቃዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ቆመልኝ
በደሙ ፡ አስተሰረየልኝ (፪x)

አዝ፦ ከእሳት ፡ ውስጥ ፡ የነጠቀኝ
በሕይወት ፡ ኑር ፡ ያለኝ
ያዳነኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x)
የራራልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው