WikiMezmur: Mezmur Lyrics:Zion Girma

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ታሪክን ሰራና፤ ታሪኬን ለወጠው እስኪ ጌታዬን ላመስግነው/3/

ከአዳምና ሔዋን በወርስኩት ሓጥያት ገና ከፍጥረቴ፤ ሳለሁ የቁጣ ልጅ የጎልጎታ ፍቅር፤ ህይወቴን ቀየረው መራራውን ሁሉ በጣፋጭ ለወጠው አዝ በሃጥያቴ ብዛት፤ የሞት ፍርድ ሲገባኝ ለኔ ሲል እየሱሴ፤ ህይወቱን ሰዋልኝ ከጨለማ አውጥቶ አረገኝ ገንዘቡ በቀራንዮ ላይ ተፈፀመ ብሎ አዝ ኑሮ አልሆን ብሎኝ፤ ግራ ተጋብቼ ነፍሴ ተጎሳቁላ እጅግ ተጨንቄ ለሞቱ አጥንቶች እስትንፋስ የሚሰጠው የናዝሬቱ እየሱስ፤ ታሪኬን ለወጠው አዝ የታሪክ ባለቤት የሆነው እየሱስ የድሃ አደግ አባት፤ ማንንም የማይንቅ ዛሬም በኛ ዘመን፤ ይሰራል ታሪክን እየሱስ ጌታ ነው የሚያሸንፍ ሁሉን