ይታይ (Yetay) - ተስፋዬ ፡ ጫላ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጫላ
(Tesfaye Chala)

Tesfaye Chala 5.jpeg


(5)

ይታይ
(Yetay)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጫላ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Chala)

 
እረጭ ፡ ጸጥ ፡ ባለው ፡ በሙታን ፡ መንደር
ሕይወት ፡ የሚሰጠው ፡ ጌታ ፡ ተሰማ (፬x) ፡ ተሰማኝ ፡ ሲናገር
አልዓዛር ፡ ሆይ ፡ ውጣ ፡ ብሎ ፡ በድኑን ፡ ጠራው
አንድ ፡ ጌታ ፡ አለ ፡ በምድር ፡ በሰማይ ፡ ሙታን ፡ የሚሰማው

የመሞቱ ፡ ዜና ፡ በሮ ፡ የደረሳቸው
ከንቱ ፡ ምሥጋና ፡ ነው??? ፡ ሳይደርቅ ፡ እምባቸው
ፈጥኖ ፡ እንደደረሰ ፡ አምላኩ ፡ ከሰማይ
ምስኪን ፡ እንደማይቀር ፡ ለዓለም ፡ ሁሉ ፡ ይታይ (፪x)

አዝይታይ (፫x) ፡ በክንዱ ፡ ደግፎ
ይታይ (፫x) ፡ እንደሚያቆም ፡ አቅፎ
ይታይ (፫x) ፡ መቃብር ፡ ይከፍታል
ይታይ (፫x) ፡ የሞተውን ፡ ያስነሳል/አልዓዛር ፡ ተነስቷል (፪x)

(ተነሳ) ፡ ሰዎች ፡ የከደኑት
(ተነሳ) ፡ የድንጋይ ፡ መቃብር
(ተነሳ) ፡ የማይሆነው ፡ ሊሆን
(ተነሳ) ፡ ሊሰራበት ፡ ተዐምር
(ተነሳ) ፡ ሊከብር ፡ ወዶ ፡ ነው
(ተነሳ) ፡ በሞቱ ፡ ሊወደስ
(ተነሳ) ፡ አልዘገየም ፡ ነበር
ኢየሱስ ፡ አልዓዛር ፡ ሲገነዝ

የደረቁት ፡ አጥንቶችን ፡ ሕይወት ፡ ዘርተው
ፍጥረት ፡ ታየኝ??? ፡ ለአምላኩ ፡ ምን ፡ ሊሳነው
መከራውን ፡ ከላዩ ፡ አራግፎታል
በእርሱስ ፡ ድንኳን ፡ ዘለዓለም ፡ ይዘመራል (፪x)

አዝይታይ (፫x) ፡ በክንዱ ፡ ደግፎ
ይታይ (፫x) ፡ እንደሚያቆም ፡ አቅፎ
ይታይ (፫x) ፡ መቃብር ፡ ይከፍታል
ይታይ (፫x) ፡ የሞተውን ፡ ያስነሳል/አልዓዛር ፡ ተነስቷል (፪x)

እኔም ፡ ታሪክ ፡ አለኝ ፡ አላዓዛርን ፡ መሳይ
በሞተው ፡ ነገሬ ፡ አምላክ ፡ ክብሩን ፡ ሲያሳይ
አራት ፡ ቀን ፡ አለፈው ፡ በቃው ፡ ሲባል ፡ ሸቶ
ትንሴ ፡ ዘራበት ፡ መቃብሬን ፡ ከፍቶ (፪x)

አዝይታይ (፫x) ፡ በክንዱ ፡ ደግፎ
ይታይ (፫x) ፡ እንደሚያቆም ፡ አቅፎ
ይታይ (፫x) ፡ መቃብር ፡ ይከፍታል
ይታይ (፫x) ፡ የሞተውን ፡ ያስነሳል/አልዓዛር ፡ ተነስቷል (፪x)

(ተነሳ) ፡ ሕይወት ፡ የሚሰጠው
(ተነሳ) ፡ ይህ ፡ ቃሉ ፡ ተሰማኝ
(ተነሳ) ፡ ከሙታን ፡ መካከል
(ተነሳ) ፡ ውጣ ፡ ብሎ ፡ ጠራኝ
(ተነሳ) ፡ ከመንፈሱ ፡ እስትንፋስ
(ተነሳ) ፡ ሕይወት ፡ እፍ ፡ አለብኝ
(ተነሳ) ፡ ነፍስ ፡ የዘራባቸው
(ተነሳ) ፡ እግሮቼም ፡ ቆሙልኝ

የደረቁት ፡ አጥንቶችን ፡ ሕይወት ፡ ዘርተው
ፍጥረት ፡ ታየኝ ፡ ለአምላኬ ፡ ምን ፡ ሊሳነው
መከራዬን ፡ ከላዬ ፡ አራግፎታል
በእኔ ፡ ድንኳን ፡ ዘለዓለም ፡ ይዘመራል (፪x)

በእኔ ፡ ድንኳን ፡ ዘለዓለም ፡ ይዘመራል (፪x)

አዝይታይ (፫x) ፡ በክንዱ ፡ ደግፎ
ይታይ (፫x) ፡ እንደሚያቆም ፡ አቅፎ
ይታይ (፫x) ፡ መቃብር ፡ ይከፍታል
ይታይ (፫x) ፡ የሞተውን ፡ ያስነሳል/አልዓዛር ፡ ተነስቷል (፪x)

ይታይ ፡ ይታይ ፡ ይታይ (፯x)