From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ለእኔስ ፡ ሕይወት ፡ በዝቶልኛል ፣ ሕይወት ፡ በዝቶልናል
ኢየሱሴ ፡ መዳኛ ፡ ማምለጫም ፡ ሆኖኛል
ኢየሱሴ ፡ መዳኛ ፡ ማምለጫም ፡ ሆኖኛል (፪x)
ሰው ፡ ሁሉ ፡ እንደመሰለው ፡ ቢያወራ ፡ ብዙ ፡ ቢናገር
ለእኔ ፡ ግን ፡ የገባኝ ፡ እውነት ፡ አረገኝ ፡ በዚያው ፡ እንድቀር
ለዚህ ፡ ነው ፡ እምቢ ፡ ማለቴ ፡ ሳይገደኝ ፡ ወጣትነቴ
የዓለምን ፡ ግብዣዋን ፡ ንቄ ፡ ወገቤን ፡ ትጥቄን ፡ ማጥበቄ
አዝ፦ አያምረኝም ፡ ዛሬ ፡ ታይቶ ፡ ነገ ፡ ሚጠፋ
አያምረኝም ፡ የዓለም ፡ ክብር ፡ ጊዜያዊ ፡ ተስፋ
አያምረኝም ፡ ይሄ ፡ አይደለም ፡ ለእኔማ ፡ ክብሬ
መኖር ፡ እንጂ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ቤት ፡ እርሱን ፡ አክብሬ (፪x)
ለእኔስ ፡ ሕይወት ፡ በዝቶልኛል ፣ ሕይወት ፡ በዝቶልናል
ኢየሱሴ ፡ መዳኛ ፡ ማምለጫም ፡ ሆኖኛል
ኢየሱሴ ፡ መዳኛ ፡ ማምለጫም ፡ ሆኖኛል (፪x)
ትውልዱ ፡ ግራ ፡ ቢገባው ፡ የዘፈን ፡ ማዕበል ፡ ቢውጠው
ነጐደ ፡ ፍጥረት ፡ ተሰዶ ፡ ገንዘብን ፡ ዓለምን ፡ ወዶ
ቀን ፡ ሲመሽ ፡ ሌቱ ፡ ሲነጋ ፡ ለአንድ ፡ አፍታ ፡ ለቤ ፡ እንዳይሰጋ
የሰማይ ፡ ደጆች ፡ ተከፍተው ፡ የአምላኬን ፡ ውበት ፡ አያለው
አዝ፦ አያምረኝም ፡ ዛሬ ፡ ታይቶ ፡ ነገ ፡ ሚጠፋ
አያምረኝም ፡ የዓለም ፡ ክብር ፡ ጊዜያዊ ፡ ተስፋ
አያምረኝም ፡ ይሄ ፡ አይደለም ፡ ለእኔማ ፡ ክብሬ
መኖር ፡ እንጂ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ቤት ፡ እርሱን ፡ አክብሬ (፪x)
የዘለዓለም ፡ ምርጫዬ ፡ ነህ ፡ የዘለዓለም (፪x)
ሙሉ ፡ ልቤ ፡ ያረፈብህ
የዘለዓለም ፡ ምርጫዬ ፡ ነህ ፡ የዘለዓለም (፪x)
ግራ ፡ ቀኙን ፡ እንዳላየው
የዘለዓለም ፡ ምርጫዬ ፡ ነህ ፡ የዘለዓለም (፪x)
አንዴ ፡ ልቤን ፡ የማረከው
የዘለዓለም ፡ ምርጫዬ ፡ ነህ ፡ የዘለዓለም (፪x)
|