From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
የከበረውን ፡ ከተዋረደው ፡ ለይቼ
ዐይኔ ፡ ተገልጦልኝ ፡ አምላኬ ፡ ያየልኝን ፡ አይቼ
ለሕያው ፡ ተስፋ ፡ ተለይቼያለሁ ፡ ወስኜ
ንቄ ፡ ትቼዋለሁ ፡ ዓለማዊነትን ፡ ጨቅኜ
በእውነት ፡ ተረትቻለሁ ፡ በእውነት
ለሕይወት ፡ ተጠርቻለሁ ፡ ለሕይወት
በፍቅር ፡ ተሸንፌአለሁ ፡ በፍቅር
ለክብር ፡ ተለይቻለሁ ፡ ለክብር
(እህም) ፡ መጐናጸፊያ ፡ ወድቆብኝ ፡ (እህ) ፡ እንድከተለው ፡ ጌታዬን
(እህም) ፡ ሞፈር ፡ ቀንበሬን ፡ ሰብሬ ፡ (እህ) ፡ ጨክኜ ፡ ትቼው ፡ እርሻዬን
(እህም) ፡ ምን ፡ ቀረኝ ፡ ብዬ ፡ ልመለስ ፡ (እህ) ፡ የያዝኩት ፡ ከእንቁ ፡ ይበልጣል
(እህም) ፡ ሰው ፡ ክርስቶስ ፡ ተገልጦለት ፡ (እህ) ፡ ዓለምን ፡ እንዴት ፡ ይመርጣል
አዝ፦ አልመለስም ፡ ወደኋላ ፡ አልመለስም (አልመለስም) (፬x)
በሆድ ፡ ሳልረሳ ፡ ከጥንቱ ፡ ያወቀኝ
በእናቴ ፡ ማህጸን ፡ ሳለሁ ፡ የቀደሰኝ
በአስደናቂ ፡ ፍቅሩ ፡ ልቤን ፡ አሸንፎ
ተክሎኛል ፡ በቤቱ ፡ በምክሩ ፡ ደግፎ
የዘለዓለሙን ፡ ተስፋ ፡ ጸንቶ ፡ የሚኖረውን
በእጅ ፡ ያልተዳሰሰ ፡ የሰው ፡ ዐይን ፡ ያላየው
ዋናዬን ፡ አግኝቻለሁ ፡ ከቶ ፡ አልመኝም ፡ ሌላ
ዓለምና ፡ ምኞቱን ፡ አላይም ፡ ወደኋላ
አዝ፦ አልመለስም ፡ ወደኋላ ፡ አልመለስም (አልመለስም) (፬x)
የከበረውን ፡ ከተዋረደው ፡ ለይቼ
ዐይኔ ፡ ተገልጦልኝ ፡ አምላኬ ፡ ያየልኝን ፡ አይቼ
ለሕያው ፡ ተስፋ ፡ ተለይቼያለሁ ፡ ወስኜ
ንቄ ፡ ትቼዋለሁ ፡ ዓለማዊነትን ፡ ጨቅኜ
በእውነት ፡ ተረትቻለሁ ፡ በእውነት
ለሕይወት ፡ ተጠርቻለሁ ፡ ለሕይወት
በፍቅር ፡ ተሸንፌአለሁ ፡ በፍቅር
ለክብር ፡ ተለይቻለሁ ፡ ለክብር (፪x)
|