አኬል ፡ ዳማ (Akiel Dama) - ታምራት ፡ ኃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታምራት ፡ ኃይሌ
(Tamrat Haile)

Lyrics.jpg


(5)

አኬል ፡ ዳማ
(Akiel Dama)

ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ኃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

አኬልዳማ የደም ምድር
እግዚአብሔር ያስብሽ በርሱ ፍቅር
አኬልዳማ የደም መሬት
እግዚአብሔር ያስብሽ በምህረት

1. የብዙ ሺህ ሠው ደም ጠጥተሻል
ያም ቢሆን ግን አልረካ ብለሻል
ዛሬሞ ትጠጫለሽ እንደውሃ
በየዳር ድንበርሽ በበረሃ

አኬልዳማ ...

2. እሾህ አሜኬላ አብቅለሻል
አመፃና ክህደት አብዝተሻል
በፍቅር በትር ነው የገረፈሽ
ይቅርታን ለምኚው ተንበርክከሽ

አኬልዳማ ...

3. ልጆችን በአደባባይ ፈጥፍጠሻል
የአዛውንቶችን ራስ ቀጥቅጠሻል
ፃድቃን አፈሰሱ የደም እንባ
እርሱ ነው በእግዚአብሔር ጆሮ የገባ

አኬልዳማ ...

4. ከአንድ ማህፀን የወጡ መንትያ
ተቃቅፈው ያደጉ ባንድ ጉያ
በጥይት ያጭዳሉ ሠው እንደሳር
እግዚአብሔር ያስታርቅሽ ከራስሽ ጋር